የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን ድምፃቸውን ማሰማታቸው ተገለፀ

የባልደራስ የስዊድን ቅርንጫፍ ያዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ፣ በስዊድን ስቶኮልም፣ የስዊድን ፓርላማ ፊትለፊትአውድማ – ወቅታዊ ትንታኔ ከአዲስ አበባ 👇https://youtu.be/yvzDwPSolqc

Posted by AbbayMedia on Sunday, October 13, 2019

አሚማ
ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

የባላደራው ደጋፊዎች በስቶክሆልም ስዊድን በዛሬው ዕለት በአደባባይ በመውጣት ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ በአሰሙት ተቃውሞ መንግስታዊ ሽብር ይቁም ፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ፤ የአብይ መንግስት አፋኝ ነው፣አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን ነች የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶችን በሰልፉ ላይ አሰምተዋል ።

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት በምክትል ሰብሳቢው ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ለገሰ ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ስለ አዲስ አበባ ቀጣይ ፋንታ እና እየገጠሟት ስላሉ ችግሮች እንዲሁም ስለባላደራው አጠቃላይ ስለ ተቋቋመለት ዓላማ በተለያዮ ከተሞች ህዝባዊ ውይይት ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ ድምፁን ለመንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥያቄዎቹን ለማሰማት በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ ቢጠራም በአስራ አንደኛው ሰዐት የከተማዋ ፖሊስ ሰልፋን በመከልከል እንዳይካሄድ አግዷል።

የባላደራ ምክርቤቱም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለህዝብ ደህንነተሰ እና ሰላም ሲባል ሰልፋን መሰረዙ ይታወቃል።

በቀጣይም ሰሜን አሜሪካ ጨምሮ በተለያዮ የአውሮፓ ከተሞች የተቃውሞ ድምፆች እንደሚሰሙ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተጠራውን ሰልፋ የባላደራው ምክር ቤት ቢሰርዘውም ፣ የሰልፉ አስተባባሪ ናችሁ የተባሉ ወጣቶች እየተፈለጉ እየታሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

1 COMMENT

 1. ትንሹ እስክንድር ወይ ኖቤል ለመሸለም ምኞት አለው ወይም በዶ/ር ዐቢይ ቀንቶአል።
  “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” ሲል የነበረው ለካንስ ውሸቱን ነው፤ ድብቅ ኣላማው ራሱን ማተለቅ ነው።
  “ባለአደራ?” አደራ ሰጭው እስክንድር ተረካቢውም እራሱ እስክንድር መሆኑ ያስቃል።
  ጓደኞቹን ሰብስቦ “ባለአደራ” አሰኝቶ ንግግር ማድረግ፣ የራሱን ፎቶ መለጠፍ፣ መግለጫ ማውጣት፣ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት፤
  ስዊድን ድረስ መሯሯጥ ምን ይባላል? ለካንስ ከርቼሌ ጽንፈኛነቱንና ትምክህተኛነቱን ሸሽጎለት ኖሯል!!
  ምን አለ አንዴ እንኳ ትልቅ አስተሳሰብ ቢታይበት? ዶ/ር ዐቢይ እኮ የተሸለመው “የኢትዮጵያ ጠ/ሚ” ተብሎ ነው!!
  በኢትዮጵያ ስም ነው! እስክንድር ገና ከመንደርተኛነትና ከጎሠኛነት አልተላቀቀም!
  ኖቤል ሽልማት ማለት በአገራችን ችግር የለም ማለት አይደለም። ህወሓት 27 አመት የጎነጎነውን ሁለት ኣመት ሳይሞላ
  ይፍታ ማለት አለማወቅ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.