ኦህዴዶችን ለስልጣን እርከብ ያበቃው አዴፓ መሆኑን አንድ የአዴፓ አመራር በይፋ ገለጹ 

የኦሮሞ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ በእሬቻ በዓል ዋዜማ ላይ በመስቀል አደባባይ ያደረጉትን ንግግር ተከተሎ ከተለያዩ ማእዘናት ከፍተኛ ተቃውሞ እየተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አቶ አሰማኸኝ አስረስ የሰጡት አስተያየት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ምክንያቱም የኦህዴድ እህት ፓርቲ የሆነው የአዴፓ ከፍተኛ አመራር አባል በመሆናቸው ነው፡፡

“እንዲያው ለመሆኑ ነፍጠኞች በከባድ መስዋትነት ይቺን አገር ባያቆዩዋት ኖሮ፣ ዛሬ እሬቻ በአዲስ አበባ ከተማ ይከበር ኖሯል?ነፍጠኞች ላባቸውን ጠብ አድርገው አዲስ አበባን ባይገነቧት ኖሮ እርስዎ መስቀል አደባባይ ቆመው ማንነተዎን ይሰብኩ ነበር?ነፍጠኞች ለዘላለም ይኑሩ!” የሚል አስተያየት የሰጡ ሲሆን።  አቶ ሰማኸኝ ፣ ያንን ተከትሎም  የኦህዴድ/ኦዴፓ ከፍተኛ አመራር የሆኑት የህግ ባለሞያው አቶ ታዬ ደንዳእ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ሺመልስ የተናገሩት ምንም ስህተት እንደሌለበት የገለጹት አቶ ታዬ፣  አቶ ሰማኸኝን በስም በመጥቀስ “አሁን ነፍጠኛ ነን የሚሉ ወገኖች እየታዩ ነው፡፡እነ አሰማኸኝ አስረስ ነፍጠኛ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በዚህ ማንነታቸው እንደሚኮሩ አስረግጠዋል፡፡መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ የነፍጠኛው ስርዓት ላደረሰው ዉድመት ተጠያቂ ባለመገኘቱና የወደፊቲ እንደሚበጅ በመታመኑ በርካታ ጉዳዮች በዝምታ ታልፈው ነበር” ያሉት አቶ ታዬ “አሁን የጉዳዩ ባለቤቶች ተገኝተዋል፡፡በህግ ሀሳቡን እናወራርዳለን” ሲሉ አቶ ሰማኸኝና ሌሎች ነፍጠኞችን ነን የሚሉትን ለመክሰስ ወይንም ለማሰር እንደተዘጋጁ ነው ለመጠቆም የሞከሩት፡፡

አቶ ታዬ ” የሰውነት ዉሃልክ መሆናቸውን ደስኩረው፤ ሌሎች ብሄሮችን በመናቅ፣ የነፍጠኝነት አጀንዳን በግላጭ አራምደዋል፡፡ ሸገርን እና አካባቢዋን በጎጃም ሰዎች ካስወረሩ በኋላ ፣ ህገ ወጥ ግንባታ እንዳይፈርስ በአቋም ተከራክረዋል፡፡ ነገሮችን ለማለዘብ ሲባል ሕገወጥነትን እና አስነዋሪ ስድብን ታግለናል፡፡ አሁን የሚበቃን ይመስለኛል …. ቢለይልን ይሻላል፡፡ ለእብሪተኞች ት እግስት ሞኝነት ይመስላል፡፡ እሹሩሩው ይበቃል” ሲሉ በጅምላም ማስፈራሪያን ማስጠንቀቂያ  አዘል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ለአቶ ታዬ ምላሽ የሰጡት የአዴፓው አመራር አቶ ሰማኽኝ  “በጣም የሚያሳዝነው ዘመኑ የመደመር ነው እያላችሁ በየአደባባዩ ትቀንሱናላችሁ: ዘመኑ የይቅርታና የፍቅር ነው እያላችሁ ሰብረናቸዋል፣ ቀብረናቸዋል  የሚል የአደባባይ ዝማሬ ታውጃላችሁ። እኛ እየተናገርን ያለነው አካሄዳችሁ እጅግ አደገኛ እንደሆነ እና መላው ሕዝብ ይህንን የተሳሳተ ትርክት አምርሮ እንዲታገለው ነው” ሲሉ በኦህዴድ አካባቢ ያለው አዝማሚያ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር አብይን ጨምሮ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የኦህዴድ አመራሮች በፌዴራል ደረጃ ከፍተኛውን ስልጣን እንዲይዙ ያደረገው በዋናነት ብ’አዴን/አዴፓ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚመረጥበት ጊዜ ሕወሃቶች አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ለመሾም ፍላጎት እንደነበራቸው፣ ነገር ኝ ብ’አዴን ከራሱ ተወዳዳሪ ሳያሰልፍ፣ ዶ/ር አብይን 100% በመምረጥ አሸናፊ እንዲሆኑ ማድረጉ በወቅቱ በስፋት የተነገረ ነው፡፡ ያ ብቻ አይደለም፣ ከዚያ በፊት በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ቢሮ በአቶ ለማና በዶ/ር አብይ አህመድ ላይ እርምጃ ለመዉሰድ ወስኖ በነበረበት ጊዜ፣ ያንን ያስቆሙት ብአዴኖች እንደነበሩም ራሳቸው ዶ/ር አብይ የገለጹበት ሆኔታ ነበር፡፡

የአዴፓ አመራር፣ አቶ አሰማኸኝ አስረስም፣ እነ አቶ ታዬ መለስ ብለው ዶ/ር አብይ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የነበረው እንዲያስታወሱ በሚል ፣ “አሁን በነፍጠኝነት የምትከሱት አማራ አቅፎና ደግፎ ከራሱ እናንተን አስቀድሞ ለዚህ የስልጣን እርካብ እንዳደረሳችሁ ዘንግታችሁ የምትሄዱበት መንገድ ከሕዝብ ተነጥላችሁ እርቃናችሁን ትቀሩ እንደሁ እንጂ ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ አይከተላችሁም:: ምክንያቱም የኦሮሞ ሕዝብ በእኩልነት መኖር እንጂ ሌላውን ለመደፍጠጥ ፍላጎት የሌለው ስለሆነ ነው” ሲሉ የኦህዴድ አመራሮች በፌዴራል ደረጃ ስልጣን ላይ የወጡት በአዴፓ እንደሆነና፣ አዴፓ ለአገር እስከጠቀመ ድረስ ማንም በሃላፊነት ላይ ቢቀመጥ ችግር እንዳልነበረው አስረድተዋል፡፡

 

2 COMMENTS

  1. Comment:
    shanqla gojam wust yale neged rasun miterabet smu enji amara alawtaletm yihn sm. Baria eritrea migegn neged rasu lerasu yawtaw meteria smu enji amara alawtaletm yihn smun. Galam hone lieloch syamiewoch bamara yeteseyemu aydelum. Metfo smoch nachew blo amara ayamnm.
    Tqit oromowoch yetezaba astesaseb ewnet asmeslew yiqbatralu. Yechat mrqana woim yebalegie tnkosa new.

  2. ምን ጥያቄ አለው! አቶ ደመቀ እራሳቸውን ከእጩነት ባያገሉና ብአዴን ድምፁን # 45ን ለዶ/ር አህመድ ባይሰጥ ኖሮ ይህ ሁሉ ዓለም 9 በኦሮሞች ዘንድ ባልነበረ ነበር! የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ናቸው ለካስ!?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.