ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን – አብርሃ ደስታ

ጓዶች በህወሓት ትእዛዝ ምክንያት ከተከራየንበት ቤት ወጥተን አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንገኛለን። በአንድ ሳምንት ውስጥ

(1) ከዓረና መቀለ ቢሮ እንድንወጣ ተነገረን።

(2) የዓረና ድርጅት ጉዳይ ሓላፊ አቶ ተክለዝጊ ወልደገብርኤል ከተከራየው ቤት እንዲወጣ ተነግሮታል።

(3) ዓምዶም ገብረስላሴ ከተከራየው ቤት አስወጥቶውት ሌላ ቤት ተከራይቶ እንደገና ከአራት ቀን በኋላ ለቆ እንዲወጣ ተነግሮታል።

(4) አብርሃ ደስታ ለሦስት ዓመታት ተከራይቶ ይኖርበት ከነበረው ቤት እንዲወጣ ተደርጎ ሌላ ቤት ተከራይቶ ቀብድ ከከፈለ በኋላ አስከልክለውት ሌላ ቀይሮ እንደገና በካድሬዎች ማስጠንቀቅያ መሠረት ቤት ተከልክሎ ለወር ኪራይ የከፈለውን ገንዘብ ተመልሶለት አሁን በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ ይገኛል። ሻወር፣ ሽንትቤት ውሃ የሌለው ቤት ውስጥ! ዓምዶምም ነገ ወደኔ ይመጣል! ግን በዚህ አንንበረከክም! በረንዳ ላይ እያደርንም ህወሓትን ከስልጣን ለማባረር በእልህና በቁርጠኝነት እንታገላለን! መኖርያ ቤት ምናገኘው በህወሓት መቃብር ላይ እንደሆነ እናውቃለን! ድል የኛ ነው!

አብርሃ ደስታ

3 COMMENTS

 1. የምትለውን ሁሉ ማመን አስቸጋሪ ነው በተደጋጋሚ ቅጥፈትህን ስለሰማነው ። አንተና አረጋዊ በርሄ ስትናገሩ ግልባጩን ተርጉሞ ከግንዛቤ መውሰድ ነው።
  የመንግስት ቤት ተቀምጠህ ቤት ክራይ ካልከፈልክ ምን እንዲያዱርግህ ትፈልጋለህ?
  በዚህ ላይ ኤሌክትሪክም አትከፍልም ሻይና እምባሻም የምትበላው እዛው ነው ኢትዮጵያ ላይም የምትዶልተው እዛው ነው።
  ስለዚህ ግብስብስ ወሬህን ይዘህ ወደዚህ አትምጣብን ምንህንም አናምንም አረጋዊን እንደማናምነው ሁሉ ማናችሁም አትታመኑም።

 2. Semere, show your real face.
  They are Ethiopiance as much as anyone in this country or maybe they have to belong your partys OLF or Tplf?
  WE THE ETHIOPIANCE BELIEVE THEM.

 3. አብረሃ we ብለህ አታወናብድ እኛ 27 አመት ስንለበለብ የት ነበርክ ኢትዮጵያዊ ከሆንክ? አንተ የኢትዮጵያን የድር ገጽ የምትፈልገው ለቀልድና የትግል አቅጣጫ ለማሳት ነው።
  ባለፈው 13 ፍየሎች ጠፉብን ብለህ ስትቀልድ ነበር ወዳጄ ይች የአረጋዊ በርሄ ቀልድ የናንተ ሰፈር ቀልድ ነችና እዛው በትግሪኝ ለትግሬዎች ንገራቸው እኛ ችግር በመፍታት ስራ ላይ ተጠምደናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.