ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

አዲስ ኤክስኘረስ / ጷጉሜ 02/ 13/ 2011 ዓም

የኦሮሚያ ቤተክሀነት ፅ/ቤት እንዲቋቋም በመጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክተርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስን በመጠየቅ የሰጠው መግለጫ ጥፋት ነው በማለት የኮሚቴው አባላት ይቅርታ እንዲጠይቁ ብፁሃን አባቶች ለማስገደድ ብሞክሩም የኮሚቴው አባላት ያጠፋነው ነገር የለም በማለት ይቅርታ መጠየቅ አይገባንም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ምክኒያቱም መግለጫ የተሰጠው፡-

1ኛ. የቤተ ክርስትያኗን ቀናኢ ልጆችን ብሶትና ፍላጎትን ለመግለፅ ነው

2ኛ. ላለፉት 27 አመታትና ከዚያ በፊት ባሉ ጊዜያት ለህዝቡ በተለይም ለኦሮሞ ህዝብ ተደራሽ ያልሆነ መዋቅርና የአገልግሎት አሰጣጠት ችግር ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ

3ኛ. ቋሚ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዳይሰጥ ከልክሏል ብለን ስለማናምን

4ኛ. ህዝቡ መግለጫውን በከፍተኛ ተነሳሽነት የሚጠብቅ ስለሆነ መግለጫው በመቅረቱ ምክኒያት የሀገሪቱ ሰላም እንዳይደፈርስ

5ኛ. እንዲያውም ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው ላለፉት አመታት ስር የሰደደውን የቤተ ክርስትያኗን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ቤተ ክርስትያኗን የፖሊትካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸው ሎሌ ያደረጉ ብፁሃን አባቶች በመሆናቸው ህዝቡን ይቅርታ በይፋ ጠይቀው ህዝቡን እንዲክሱ በትህትና በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን:: በአጠቃላይ በእነዚህና አያሌ አሳማኝ ምክኒያቶች ያለጥፋታችን ይቅርታ ጠይቁ የተባልነውን አስገዳጅ ኣካሄድ አልተቀበልንም፡፡

የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ
ጳጉሜ 2፣ 2011 ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.