ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ይዘው አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን እስር ላይ የነበሩ 105 ኢትዮጰያውያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

105ቱ ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ሱዳንን መተላለፊያ በማድረግ ወደ አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ ለመግባት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በሱዳን እስር ቤት ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምበሲ ተጠልለው የቆዩ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ከእስር የተለቀቁት ዜጋን ያስቀደመ ዲፕሎማሲ በመከተል መሆኑም ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓትን አጠናቀው ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን ይዘው አዲስ አበባ የገቡት፡፡

ከእስር ተፈተው አዲስ አበባ ከገቡት መካከል በርካታዎቹ ሴቶች መሆናቸውም ተገልፀዋል፡፡

የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ሉዓላዊ ምክር ቤት መመስረት መቻላቸውን ተከትሎ በርካታ ሱዳናውያን ለዶክተር ዐቢይ አህመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በደረሱት ስምምነት መሰረት የልዑላዊ ምክር ቤት የሚቋቋም ሲሆን፥ ምክር ቤቱ ስድስት የሲቪል እና አምስት ወታዳራዊ አመራሮችን በአባልነት ያካትታል፡፡

የልዑላዊ ምክር ቤቱን ሁለቱ ወገኖች በየሶስት ዓመት እየተፈራረቁ የሚመሩት ሲሆን፥ በዚህ መሰረት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የነፃነትና የለውጥ ሀይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሾም ይሆናል፡፡

በዚህ ስምምነት ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩልላበረከተችው ከፍታ አስተዋ ሱዳናውያኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአልዓዛር ታደለ እና ምስክር ስናፍቅ

(ኤፍ.ቢ.ሲ

2 COMMENTS

 1. ይህ በራሱ ጥሩ ነው። ግን “የራሷ አሮባት የሰው ታማስል”የሚለውንም ብሂል አለመርሣት ነው።እዚህ እነጃዋር ምንቅርቅራችንን እያወጡ ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ መሆን ውዳሤ ከንቱን የመሻት አባዜ ነው።

 2. ግሩም፣
  አንተ ወይም ዘመድህ ታስረው ቢሆን ዶ/ር ዐቢይን ሰማይ ታወጣቸው ነበር!
  ዶ/ር ዐቢይ በዓመት ተኲል ህወሓት 27 ዓመት የተከለውን አረም ነቅለው አዲስ አበባ እንዲተክሉ አስበህ ከሆነ ምኑም አልገባህም ማለት ነው።
  እነ ጀዋር፣ እክንድር፣ ሰርፀ፣ አቻሜለህ፣ ወዘተ አክራሪ ናቸው። ሰፊው ሕዝብ አይፈልጋቸውም፣ ችግር አይፈጥሩም ማለት ግን አይደለም።
  ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ዋነኛ ነገሮች እየተሠሩ ናቸው። ህወሓት ይፍጨርጨር እንጂ መቀሌ እስር ቤት ገብቷል። ሕዝብ አንቅሮ ተፍቶታል።
  “ዲጂታል ወያኔ” ብሎ በየድረገጹ ስም የሚያጠፉ፣ ሕዝብ ለማባላት የተነሡ ካድሬዎችን አሠማርቷል። አንተን ከዚያ አልመድብህም። ያንተ
  አለማወቅ ወይም ቶሎ ቶሎ ለውጥ ለማየት ከመጓጓት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.