የጠነጠንክ ሁን ልጅ ገላ! (በላይነህ አባተ)

ራስ በቅማል የሚያስልስ፣
ደካማ አትሁን ልፍስፍስ!

መከላከያህ  ሲቀጥን፣
ቅማልም ወሮ ገላህን፣
ያሳክክሃል  በሸቀን!

ቅማል ሲመጥህ ደምህን፣
ጥፍርህ ያቆስላል ቆዳህን!

ጥፍርህ ቆዳህን ሲያቆስለው፣
ለጀርሞች ሰርግ ድግስ ነው!

ጣትህ ቆዳህን ሲዠልጥ፣
ጀርም አካልህን ወሮ ቁጭ፡፡

ልጅ ገላ በአንክሮ ስማ፣
ለደቂቃ አትሁን ደካማ፣
ለተባይ አትሁን ሰለባ!

ተባዩ ወሮ ሲበላህ፣
ቆዳን በጥፍር መላጥህ፣
መፍትሔ ፍጡም አይሆንህ፡፡

አቅም እያለህ ጠንካራ፣
የቅማል እከክ ማዳኛ፣
ገላን በጣቶች አታድማ!

ወራሪ ቅማል ሲበላው፣
ገላህን ጣትህ ቢያቆስለው፣
ገዝግዘህ ቆርጠህ አጥለው!

አስብ እባክህ ልጅ ገላ፣
ማሞን አትሁን ተላላ፣
ቆዳህን በጣት አታድማ!

ራስህ እንዲሆን የጠዳ፣
ተቅማል ተጀርም ወረራ፣
ተሸቀን ቆዳ በሽታ፣
መከላከያህን አበርታ!

ቆዳን በጥፍርህ ሳትቆፍር፣
እከክ አምጪውን መነጋግል፡፡

ለጀርም ለተባይ መጋኛ!
ለአካሎችህ ግን መዳኛ!
መከላከያህ የጠና!
ብረት መዝጊያ ሁን ጠንካራ!

ጀርሞች አይወዱ ደካማ፣
የጠነጠንክ ሁን ልጅ ገላ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ሰኔ ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.