በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች አቃቂ ግቢን ለቃችሁ ውጡ በመባላቸው ለችግር መዳረጋቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አቃቂ ግቢ የሚኖሩ የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ግቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚል መመሪያ በማስተላለፉ ለችግር ተዳርገናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ።

ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡት ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲው ውል ገብቶ የተቀበላቸው የማደሪያ አገልግሎት አካቶ ቢሆንም ማደሪያውን ልቀቁ ማለቱ አግባብ አይደለም ይላሉ።

ተማሪዎቹ ግቢው ለትምህርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ያሟላ በመሆኑ መልቀቁ በትምህርታቸው ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳን ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩሉ ዩኒቨርስቲው ለተማሪዎች ማደሪያ ለመስጠት የገባው ውል አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹን ልቀቁ የተባሉት የመኖሪያ ግቢው ባለቤትነት ብሄራዊ ባንክ ግቢውን ለራሱ ጉዳይ በመፈለጉ እንዲለቀቅለት ጥያቄ በማቀረቡ እንደሆነ ግልፀዋል፡፡

እንዲሁም ወቅቱም የእረፍት ጊዜ እና ክረምት በመሆኑ ተማሪዎች እንዲለቁ መወሰኑን ነው የተናገሩት፡፡

የሚቀጥለው አዲስ የትምህርት አመት ሲጀመርም የራሱን ህንጻ እያስገነባ በመሆኑ ከክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ቅድሚ በመስጠት ለተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በትእግሰት ስለሺ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.