ኢትዮጵያ የሱዳን ውጥረትን ለማርገብ ባደረገችው ጥረት አድናቆት ተቸራት

ኢትዮጵያ በሱዳን የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ባደረገችው ጥረት በኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ አድናቆት ተቸራት፡፡

68ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

ለአንድ ቀን በአዲስ አበባ የተካሄደው 68ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ በሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ዝርዝር ውይይት አካሂዶ ውሳኔ በማሳለፍ ነው የተጠናቀቀው።

ጉባኤው የሱዳን ሰላምና አንድነት በአካባቢው አገሮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን በማንሳት የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት ያካተተ መፍትሄ ሊበጅ እንደሚገባ ገልጿል።

በአገሪቱ ሰላምን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ከተለያዩ ወገኖች ከሚደረግ የተናጥል ጥረትና ጣልቃ ገብነት ይልቅ ሁሉንም የፖለቲካ ሃይሎች ያለአድሎ ያሳተፈ አካታች የሰላም ጥረት መከተል እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።

ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ካርቱም በማቅናት ከሁለቱም ወገኖች ጋር ባደረጉት ውጤታማ ውይይት መሰረት ውጥረቱን ለማርገብ መቻሉ በጉባኤው አድናቆት ተችሮታል።

ቀጣይ የድርድር ሂደቱን ለመደገፍ ልዩ መልዕክተኛ በመሰየም ጠቅላይ ሚንስትሩ ያደረጉት ገንቢ ጥረት ውጤታማ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ ይሄው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ኢጋድ ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ በጉባኤ ማጠቃለያ አረጋግጧል።

ጉባኤው በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ጋር በተያያዘ ባደረገው ውይይት ጁባ ተካሂዶ በነበረው 67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ስብሰባ ወቅት በተደረሰው ስምምነት መሰረት አፈፃፀሙን ገምግሟል።

በዚህም መሰረት በደቡብ ሱዳን በቀሪው አምስት ወራት መከናወን የሚገባቸው ስራዎች በተመለከተ አባል አገራትና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፉን አጠንክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

የአገሪቱ መንግስትና ተቃዋሚ ኃይሎች ለስምምነቱ ተግባራዊነት በበለጠ ቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጉባኤው አሳስቧል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርና የወቅቱ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጉባኤው ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር የአባል አገራት ሚኒስትሮችና ተወካዮዎች ለጉባኤው በስኬት መጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

2 COMMENTS

 1. ” ኢትዮጵያ የሱዳን ውጥረትን ለማርገብ ባደረገችው ጥረት አድናቆት ተቸራት ”

  There is this proverb: የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች

  Abiy is agent of ferenjis and arabs

  Abiy is evil

  Abiy is tribalist

  Abiy is anti-Ethiopian

  Abiy is a traitor

  Abiy is a liar

  .

  .

  .

  Instead of first taking care of problems in Ethiopia, this foreign agent travels abroad to solve others people’s problems. Actually anti-Ethiopian Abiy is preventing problems from being solved, as this info shows:

  በየከተማው ሰልፉን በሚያካሂደውና ለውጡ ፈላጊው ሕዝብና ለውጡን በሚመሩት የመንግሥቱ ክፍል መካከል ክፍተት ተፈጥሯል። ለምሳሌ፤ የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር በሰንደቅ ዓላማችን ላይ ያስቀመጠውን ምልክት ጥለው፤ አረንጓዴ፣ ብጫና፣ ቀይ ቀለማት ብቻ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፤ ሕዝቡ እያውለበለበ፤ “ተደምሬያለሁ!” እያለ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም እያሞገሰ ወጥቷል። ነገር ግን፤ የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባርን ሰንደቅ ዓላማ ለማስከበር፤ መንግሥታዊ መዋቅሩ፤ እኒህን አውለብላቢዎች እያሰረ ነው። ሕዝቡ ቀድሞ፤ “አንለያይም!” “አንድ ነን!” “በዘር አጥር መከፋፈሉ ያብቃ!” “ኢትዮጵያዊ ነን!” እያለ ነው። አሁንም በየክልሉ ያሉትን መሪዎች ይሄ የሚጋፋቸው ሆኗል።

  Source: ethioforum dot org

  This news from IGAD is supposed to promote the anti-Ethiopian and foreign agent Abiy. Perhaps he requested or even bribed IGAD for the release of this news. This is PR, and also interference in Ethiopian politics.

  Don’t be fooled guys.

  We should rather demand the immediate resignation of the tribalist and ferenji puppet Abiy government.

 2. Abiy has to find solution for the ethiopian children , women, elderly people …. thrown out on the street by opdo thugs who are demolishing houses in and around addis abeba. these thugs are saying the houses are built illegally. to start with, the rotten opdo cadres who are corrupt to the core have no ground to stand and accuse poor citizens as illegal. these cadres themselves live in houses illegally owned by corruption, they are thieves who have made themselves rich by corruption. the whole system is a corrupt system from top to bottom and it is a disgrace that poor people are being kicked about like a football in this manner while the real criminals continue to cause misery and hardship on ordinary citizens.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.