የደደቢትና የፋሲል ከነማ ጨዋታ በረብሻ ተቋረጠ!! 

በመቀሌ ስታዲየም ሲካሄድ የነበረው የደደቢት እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ በፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ላይ በፋሲል ከነማ ተጨዋቾችና የቡዱኑ አባላት ላይ ድንጋይ በመወርወሩ ጨዋታው በ69ኛው ደቂቃ ተቋርጧል፡፡ ጨዋታው እስከተቋረጠበት 69ኛዉ ደቂቃ ድረስ ፋሲል በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘውን ደደቢት 4 ለ 0 እየመራ ነበር፡፡ በተጫዋቾችና ቡድን አባላት ላይ የደረሰ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦች ከዚህ ቀደም በወልደያና አዲግራት ከተሞች ከተከሰቱት የደጋፊዎች ግጭቶች ጋር በተያያዘ ጫዋታቸውን ሲያደርጉ የነበረው በገለልተኛ ሜዳ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ከሁለቱ ክልሎች ፕሬዝደንቶች ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሜዳቸው መጫወት ጀምረው ነበር፡፡ ይህ ድርጊት በፌደሬሽን የስፖርት ጨዋነት ደንብ ምን አይነት ቅጣት እንደሚያስከትል ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ከአሁኑ የመቀሌው ስታዲየም ድርጊት ጋር በተያያዘ፤ በቀጣዩ ሳምንት ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከፋሲል ከነማ ጋር በጎንደር ዓፄ ፋሲል ደስ እስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተመሳሳይ ችግር ሊከሰት ይችላል የሚል ሥጋትንም አሳድሯል፡፡
#ምንጭ፦ Andafta.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.