“የአዲስ አበባና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሠራበት ያለ ጉዳይ ነው…” (Interestingly Unusual Frankness) (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

በአጠቃላይ የኢትዮጵያም ሆነ በተለይ የአዲስ አበባ ዕጣ ፋንታ በተሳለጠ ሁኔታ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተጓዘ ይመስላል፡፡ 99 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ጥልቅ ዕንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ዕንቅልፉን ቢለሸልሽለም ታሪክ ግን ጉዞውን አያቋርጥምና መረረንም ጣፈጠንም የሀገራችን መፃዒ ዕድል የሚወሰንበት ወሳኝ የጡዘቶች ጫፍ ላይ ደርሰናል፡፡ መርዶም ይሁን የምሥራች በራችንን ሊያንኳኳ ተቃርቧል፡፡ ሕወሓትና ጌቶቹ የቀበሯቸው ቦምቦች ሁሉ ሊፈነዱና በመጨረሻው አርማጌዶ ውሉ ሊለይ ጊዜው ደርሷል፡፡

ይህች ወቅት ለኢትዮጵያውያን ልክ እንደሰሙነ ህማማት ብትቆጠር አይበዛባትም፡፡ ጥቂት የማንባል ዜጎች በቀንም ሆነ በሌሊት የኅሊና ዕረፍትና የአልጋ ላይ ዕንቅልፍ አጥተናል – በ“ምን እንሆን ይሆን?” መሳቀቅ፡፡ ዘጠኝ ሞት ቢመጣ አንዱ መግባቱ ለማይቀረው ስለኛ ብቻ ሣይሆን ስለመጪው ትውልድ በመጨነቅ የባዘነ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን፡፡ በዚህም ምክንያት ሌሊቱን አንዳንድ የድረ ገፅ የመረጃ ምንጮችን ሳገላብጥ አድሬ አሁን ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም፡፡ ጥቂት ሃሳቦችን ልሰንዝር ብዕሬን ያነሳሁትም ለዚህ ነው፡፡

አቻምየለህ ታምሩ በአጭሩ ያስቀመጣቸው ዕይታዎቹ ስበውኛል – ከሣተናው ድረ-ገፅ እንዳነበብኩት፡፡ (https://www.satenaw.com/amharic/archives/63906)

ሕወሓትና ኦህዴድ አያ ዲያብሎስ በአንድ ምጣድ ያሰፋቸው በተለመደው አገላለጽ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎችና በጠባይም በምግባርም አንድ አካል አንድ አምሳል መሆናቸውን በወቅታዊ ምሣሌ አስደግፎ አቻምየለህ በዛሬ ሌሊት ቅልብጭ ያለች አጭር መጣጥፉ አስረድቷል፡፡

ወደ ቀጣዩ አንቀጽ ከመሸጋገራችን በፊት ከዚህ በታች ያስቀመጥኳትን ብሂል አጢኑልኝም፡፡

እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ፤
እዚህ ማዶ ሁኖ ክፉ ሰው ወይ አለው፤
ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

ማሌሊት ማነው ሕወሓት ሰሞኑን መግለጫ አውጥቷል፡፡ መጋቢት 17 ቀን 82 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ደራ ከተማ ላይ ከምርኮኛ ወታደሮች ጠፍጥፎ የሠራው ልጁ ኦዴፓም እንደዚሁ፡፡ የሁለቱም መግለጫዎች በፉከራና በጦርነት ዐዋጅ የታጨቁ ናቸው፡፡ ሁለቱም ድርጅቶች ኢትዮጵያን በሸጥና በጎጥ በታትነው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ለማስደሰትና በርዕሰ አድባራት ሊቀ ሣጥናኤል አማካይነት ወደር ለሌለው ጀግንነት እንዲሰጥ የተዘጋጀላቸውን የታላቅ ጀብዱ ሊሻን ለመቀበል የሚራወጡ ናቸው፡፡ ሕወሓት ለይቶለት የኢትዮጵያን ስም መጥራቱን ቢጠየፍም ኦዴፓ ግን በአዲስ ሥልት በሚያቀነቅነው “እምዬ ኢትዮጵያ” በሚለው ዘፈኑ ብዙዎችን እያነሆለለ  ውስጥ ለውስጥና አሁን አሁን ደግሞ በግልጽ ሀገራችንን የማፈራረሱን ሥራ በገሃድ እያከናወነ ነው፡፡

በርዕሴ ላይ ያስቀመጥኩት የአማርኛው ክፍል በግልጽ የሚናገረው የሚከተሉትን የኦህዴድ ተግባራት ነው፡-

 1. (በነሱው አጠራር) ፊንፊኔን ከአማራ ለማጽዳት የጀመርነውን ፈጣን እንቅስቃሴ በስፋትና በጥልቀት እንቀጥላለን፡፡ ከዚህም አንጻር –
  • በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮችን ከየመሥሪያ ቤቱ እየመነጠርን እንዳንሳፈፍናቸውና በኛ ጎሣ አባላት እንደተካናቸው ሁሉ አሁንና ወደፊትም ይህን ተግባር በሚያስደምም ፍጥነት እንቀጥላለን፡፡ የወያኔን የ27 ዓመት ድካምና ልፋት የሚያስንቅም ድል በቅርብ እናስመዘግባለን፡፡ ስለዚህ በግራም በቀኝም ያላችሁን ደጋፊዎች በኛ ኩሩ፡፡
  • በፊንፊኔ ዳርቻዎች የጀመርነውን የአማራና የሌሎች ጎሣዎችን መኖሪያ ቤቶች በግሬደር የማፈራረሱን ተግባር ቀጥለን ነገና ነገ ወዲያ መሀል ከተማ የሚገኙትን የኦሮሞ ያልሆኑ ቤቶችና ሕንጻዎችን እንገነዳድሳለን፡፡ (ልብ አድርጉ በነዚህ ሁለትና ሦስት ቀናት ብቻ በለገጣፎ አካባቢ ወደ አራት ሽህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች እንደፈራረሱ በሣተናው አንብበናል፡፡ አስቡት – አራት ሽህ ቤት እያንዳንዱን በአምስት የቤተሰብ አባላት ብታባዙት 20 ሽህ ሰው በአንድ አዳር ጎዳና ወጣ፤ ሀብት ንብረቱም በግሬደር ተጨፈላለቀ፡፡ አራት ሽህ ቤት ማለት በከተሞች ብያኔ የሁለት ከተማ ሕዝብ ማለት እንደሆነም መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የኦዴፓ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊነት እንግዲህ በዚህም ይገለጻል፡፡ ዘርን ካጸዱ አይቀር እንዲህ ነው፡፡ ጎበዞች!! ያበጠው ይፈንዳ እንጂ ኧረ በርትታችሁ ቀጥሉ፡፡
  • ባንኮችን፣ አየር መንገድን፣ የገንዘብ ተቋማትን ወዘተ. በመቆጣጠር ለኦሮሞ ባለሀብቶች የምናደርገውን  ከወያ የተማርነውን አድልዖ በስፋት እንቀጥላለን፡፡ (ይህም የጠ/ሚኒስትሩን አንደበታዊ አቀራረብና በተግባር ግን ምን እየተከናወነ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በሀገራችን ውስጥ እነሼክስፒርንና ዳንቴን የሚያስከነዱ ጸሐፌ ተውኔቶችን መፈልፈል የሚጠቁም ነው፡፡)
  • ከዚህም በተጓዳኝ ልክ እንደወያኔዎች ሁሉ የአዲስ አበባን የሕዝብ አሰፋፈር ለመለወጥ እስካሁን ብቻ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠሮች እያመጣን የአዲስ አበባ ኗሪነት መታወቂያ አድለናል፡፡ ገና ደግሞ እንቀጥላለን፡፡ ( በአንድ በኩል ሌሎችን መንቀል – በሌላ በኩል የራስ የሚሉትን ዜጋ ከጠቅላይ ግዛ እያመጡ መትከል፡፡ ይቺ ናት ወያኔያዊ ጨዋታ ማለት፡፡ ወያኔም በወልቃይት፣ በራያና በአፋር እንዲሁም በአዲስ አበባ ያደረገው ይሄንኑ ነው፡፡ ጎረምሳ ዝንጀሮ ያባቱን ኮቴ ከኋላው እየተራመደ ለክቶ እኩል ሲሆንለት ያባቱን ሚስት እናቱን ቀምቶ እንደሚያገባ ሁሉ ኦህዴድም እያደረገ ያለው ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ በቡዳ ቤት ሰላቢ ገባና ትያትሩ ጦፈልህ፡፡ ዝም ብለህ መጨረሻውን ብቻ ማየት ነው፡፡)
 2. ይሄ ፌዴራላዊ ሥርዓት እንደፌዴራል ሥርዓት ተቆጥሮ ሞቶ ኦህዴድም አቅም አገኘሁ ብሎ ልክ እንደወያኔ “ሥርዓቱ የሚለወጠው በመቃብሬ ላይ ነው፤ በርሱ መጣችሁ ማለት ባይኔ መጣችሁ ማለት ነው” እያለን ነው፡፡ በወረት ፍቅር ከናወዘ ጎረምሣ ዝንጀሮ ከዚህ በላይ አይጠበቅም፡፡

በጥቅሉ ይህ ወቅት ብዙ ነገሮችን አጉልቶ እያሳየን ነው፡፡የፖለቲካ አሰላለፎችም እንዲሁ ግልጽ ሆነዋል፡፡ ማን የማን ጥገኛ እንደሆነ ተለይቷል፡፡ ማን እፍኝ ለማትሞላ ምሥር እንዳደረና ወንድሙን ይሥሃቅን (ሀገርን) እንደሸጠ፣ ማን ለፍርፋሪ ሥልጣን እንደተንበረከከና ወገኑን እንደካደ፣ ሀገራዊ ራዕዩንም አሽቀንጥሮ እንደጣለ፣ማን በአስመሳይነት ካባ ተጀቡኖ ቀን ቀን “ኢትዮጵያ፣ ኢትየጵያ” እያለ ማታ ማታ ከዘረኞችና ከከፋፋዮች ጋር ባንኮኒ ላይ ዊስኪውን እንደሚጨልጥ እየተረዳን ነው፡፡

አሰላለፋችን በሚዲያውም እየለየለት ነው፡፡ በዚህን ወቅት ስለኢትዮጵያ መዘመርን እንደወንጀል የሚቆጥሩ የአንድነት ኃይል ነን ባዮችን እያየን ነው፡፡ እንደጓድ ቆምባጫምባው መሆን አምሮኝ ወይም ፈልጌ አይደለም፡፡ ምሣሌ ለመስጠት ያህል ነው፡፡ አዎ፣ ለምሣሌ ይህችን ጽሑፍ በሚዲያው የሚያወጣት ኢትዮጵያዊ ነው ወይምና ቢያንስ የሃሳብን በነፃነት መንሸራሸር የሚደግፍ ዴሞክራት ነው፡፡ የሚያፍናት ግን ወያኔና ወያኔያዊ ባሕርይ የሚያሰቃየው ነው ወይም የሃሳብን  በነፃነት መንሸራሽር የሚጠላ አፋኝና አምባገነን ነው፡፡ ከዚህ የሚያልፍ ነገር የለም፡፡ ስለዚህም አሰላለፋችን ከዚህም ይነሳል፤ ከዚህም ይፈረዳል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሀሰት ከተነገረ በተፈለገው ሁሉ እምላለሁ፡፡ ይህን ጽሑፍ የማያስተናግዱ እደግመዋለሁ ኢትዮጵያውያን ነን ማለት ሊያሳፍራቸው ይገባል፡፡ ለገጣፎ ላይ 4000 ቤት፣ ቤተ መንግሥት አጠገብ ብዙ ቤት፣ በፉሪና በላፍቶ እጅግ ብዙ ቤት እየፈረሰ፣ ፖለቲካው ከቀን ወደ ቀን እየተግማማና ወደ አንድ ወገን ያጋደለችው መርከብ ልትገለበጥ አንድ ሐሙስ ብቻ በቀረበት ሁኔታ ዝም ጭጭ የሚል የፖለቲካ ድርጅትና ሚዲያ ከአድር ባይ አዘጥዛጭ ተለይቶ አይታይም፡፡ በአፍ የሚሉትና በብቅል ቀን የሚወሻክቱት እየተደበላለቀባቸው የሚቸገሩ ወገኖች እንዳሉም እየተረዳን ነው – በዘር ጥላቻ የታወሩ ጭምር፡፡ እነዚህን አስተኔ የሌሊት ወፎች ታሪክ ዋጋቸውን እንዲከፍላቸው ከመጸለይ በስተቀር የምንለው የለም፡፡ ወይም ከወዲሁ ልብ ይስጣቸው፡፡ የሚገርም የነገሮች አካሄድ ውስጥ እንገኛለን፡፡ የዓላማ አንድነት መገለጫው ብዙ መሆኑንም በእግረ መንገድ እያስተዋልን ነው፡፡

ለማንኛውም ያቺ መከረኛ ሴተኛ አዳሪ አለች የተባለውን መጥቀስ ፈልጌ አሁን ጠፋኝና ተውኩት፡፡ ዘንድሮ ይለያል ጉዱ፡፡ አዎ፣ ኢትዮጵያን አጭበርባሪ እስከወዲያኛው አጭበርብሯት አያውቅም፡፡ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ እረኛ በጎጠኞች የሚሸነፍበት አንድም አመክንዮም የለም፡፡

ግን እባካችሁን ስንጣላ እንደምንታረቅ ሆነን እንጣላ፡፡ ስንነጋገር እንደምንግባባ ሆነን እንነጋር፡፡ መቅኒ ውስጥ ገብቶ ከትውልድ ወደ ትልድ እየተላለፈ የሚያመረቅዝ መጥፎ ነገር ከሠራን እኛን ብቻ ሣይሆን ልጆቻችንንም እንጎዳለን፡፡ ወያኔ በተለይ በአማራ ላይ የሠራው ግፍና በደል ከዚህ አንጻር የሚታይ ነው፡፡ አማራንና ወያኔን ለማስታረቅ ልነሳ የሚል ምድራዊ ኃይል የሚፈራው እንግዲህ በአማራ በደረሰው ተዘርዝሮ የማያልቅ የፈሪ ዱላ ዓይነት ወያኔዊ ሰቆቃ ሳቢያ ነውና ከአሁን በኋላ ጉልበተኝነት የሚሰማው ቡድን ጉልበቱን በጠበልም ይሁን በሥነ አእምሮ ህክምና ሰከን እያደረገ በቅጡ እንዲበድል – መበደልም ካለበትና ካማረው – ራሱን ያርቅ፤ ያስተካክል፡፡

በተረፈ ዐውድማው በየአቅጣጫው እየተለቀለቀ ነው፡፡ በቅርቡ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆን በጉጉት ይጠበቃል፡፡ በሬዎቹም ወደየዐውድማቸው በመሠማራት ላይ ናቸው፡፡ በኮረም በኩል ለምሣሌ የተሰማ የጦርነት ጥንስስ ዜና አለ (https://www.satenaw.com/amharic/archives/63877)፡፡ ሁሉም ይሰናዳ፡፡ መቀመጥ መቆመጥ ነው – ምን ይፈይዳል? እህል መጨረስ ነው፡፡ ሰላም ምን ይሠራል? አዎ፣ ጎራዎችም በፀጥታ ብዛት ደንቁረዋል፡፡ የባሩድ ሽታም ናፍቋቸዋል፡፡ ልክ ነው፣ ብንራብ ብንጠማም መለከቱ ይነፋና ወንድና ሴቱ ይለይ፡፡ ከሁልጊዜ ፈስ ደግሞ የአንድ ቀን ምንትስ እንደሚሻል ግልጥ ነው፡፡ ሁልህም ታጠቅ፤ ዝመት፤ ባባቶችህ ወኔም እርስ በርስ ተፋለምና ሀገርህን የጃርት መፈንጫ አድርጋት፡፡ ያ ነው ጀግንነት ማለት! ቀን ሲሰጥህ በወንድሞችህ ጫንቃ ላይ ቆመህ ነው ማስጨነቅ፡፡ አለዚያ ወንድነትህ እንዴት ይታወቃል? ምኑንስ ተወልደከው! ለማንኛውም ታዲያ ርብን ጠብቃት፤ መሀል ሸዋንም አትርሳት፡፡ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ባሌ … ክምርህን ከሚገነብሩ ወጣት ዝንጀሮዎች ሰብልህን ጠብቅ፡፡

መረሳት የሌለበት ግን ወያኔ ለአማራ ብላ የረጨቻቸው መርዞች፣ ያቆመቻቸው አፓርታይዳዊ ምሠሶዎች ሁሉ ለተጋሩም የሚተርፉ መሆናቸው ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው “ለሰው ጉድጓድ ስትቆፍር አታርቅ” የሚባለው፡፡ የጥቃቅን ፌዴራል ተብዬ መንግሥታትን ሀብትና ገንዘበስ ማን ነበር የሚዘባነንበት? የዘሩትን ማጨድ ያለ ነው፡፡ አሁን መሀል ሜዳ ቆሞ መጨነቅ ዋጋ የለውም – መጋፈጥ እንጂ፡፡ መጥኖ መደቆስ ዱሮ ነበር፡፡ ቻው ቻው ወያኔ፡፡ ቤት ለእምቦሳ ኦህዴድ!…

አለቃ ገ/ሃናም “ማዘንጊያ፣ እዚያም ቤት እሳት አለ” ያሉትም ለዚህ ነው፡፡ አሁን በውነቱ ከትግሬና ከአማራ ብዙ የሚያጣው ማን ነው? ባለፉት 27 ዓመታት መሬቱን፣ ወርቁን፣ ሕንፃውን፣ ገንዘቡን፣ ምኑን ምናምኑን ሱቅ እንደገባ ሕጻን በስግብግብነት ሁሉንም ያጋበሰው አማራ ነው ወያኔ? እናስ ማን ይሆን ይበልጥ የሚጎዳው? “ባመጣኸው ዳኛ ትሆን እሥረኛ” ማለትም አሁን ነው፡፡

ልናይ አይደል? (ma74085@gmail.com)

13 COMMENTS

 1. Fake ethiopianism! This guy try to tell us who has full rights to decide on our fate in Ethiopia. He claims that only Amaharas and the amaharanized Ethiopians can decide on fate of the whole Ethiopians. For him the only God given language in Ethiopia is Amaharic.

  The term OLF defines the struggles and endeavors of the whole Oromo nation for its freedom and emancipation. It has great and very meaningful values for the Oromo people in general,  and for the QEERROOS in particular. It stands for all oromo organizations – ODP, ODF, OFC and all factions of the OLF itself. It is comprehensive. The political values of the OLF are written not only on the paper, but also in the hearts of the whole Oromo people. 

  The struggles of the Oromo heroes and heroines have exposed the falsehoods of the fake Ethiopia nationalism. The Oromo intellectuals have reactivate and reasserte the Oromo nationalism (OROMUUMA). All the Oromo are now proud of their cultural heritages, history and  social values.

  There is nobody without national background and heritages in this planet. All human beings have ethnic backgrounds regardless of the composition of their ethnicity. Those who try to nullify their ethnic backgrounds are claiming Amhara ethnicity by default under the mask of Ethiopianism. They speak amharic and claim the cultures from north as their culture. They try to impose their default identity (Amaharaism as Ethiopianism) on the others. But it is not acceptable! Therefore, the current Ethiopian nationalism is equivalent to the Amahara nationalism. Which will be voided soon. It will be replaced by the multinationalism of all Ethiopians. You should have to swallow this truth.

  The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more in Ethiopia. But now temporally you can make noise here and there. That is all what you can do right now.

 2. Dear Gamadaa and others who are suffering from inferior complex.
  I tell you this very earnestly that any language is not different from the pen in your pocket or the laptop you may have. You and your likes are simply stricken by the so called psychological disease known as schizophrenia. No body can help such disease except perhaps death which I do not recommend it for you, my beloved compatriot, son of Ethiopia.
  You see, there about 71016 or so languages on this planet. I wish I speak all of them but I can’t. Evene if I am given thousands of years here on earth, I can speak even 5 percent of them. You speak one language today, maybe you, I mean your coming generations, may speak another language after 100’s of years later. It is common to speak this or that language. For example, I can speak Tigrigna, Italian, Ge’ez, English, and am learning currently OromiFfa, because every language is mine. You can’t give or dis-give me Oromiffa as you claim to be so, I mean, Oromo. Oromonet is RATHER a choice, not a must. You happened to be born in one of Oromifa speaking people. They may not in reality be Oromos. Anyone can be Amhara. There is no fence among ethnics like you and your likes believe so. Ethnicity is not a religion, dear me, I mean you are me in Christ and in every aspect. Let’s come to the center, the hub of human being(s). We were only one, Adam; it is due to stupid people that we are immersed in an abyss of eternal conflicts for the sake of satisfying their egos. Money, sex, and power. I hope you understand me well. I myself am an Oromo distraction, if you really trust my words. I gain no penny in lying.

 3. ወያኔ በኣጀንዳው የያዘውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ተንኮሉ ባሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በሚመራው መንግስት በኩል አየተገበረው አንዳለ ከማንም የተሰወረ ኣይደለም፥፥ የዛሬ ፰ ወር ገደማ ህዝብ ድጋፉን የገለጸው ብሔራዊ እርቅና የሽግጝር መንግስት አቋቁሞ በእኩልነት በፍትሕና በውነተኛ ዲሞክራሲ ላይ የተገነባች ኢትዮጵያን መስርቶ ሁሉም ከህግ በታች ሆኖ በዘር ሳይከፋፈል የሃገሪቷ አንጡራ ሃብት በግለሰቦች እጅ ሳይመዘበር፥ አንዱ በውስኪ ሲራጭ ሌላው የሚጎርሰው አጥቶ የማያለቅስባት፥ ሰው የተሰማውን በመንግስት ላይ ቅር የተሰኘበትን ነገር ለመናገር ለመጻፍና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በነጻነት ያለፍርሃት ለማካሀድ የሚችልባት፥ መሪዋ በህዝብ፥ ከህዝብና ለህዝብ አገልግሎት የሚመረጥባት፥ መሪዎቿ ጋራ እንደናደ ዝንጀሮ በቴሌቭዥን እየቀረቡ በ፺ሚሊዮን ህዝብ ላይ የማይደነፉባት፥ መከላከያው ሰራዊት የገዢውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ሎሌ ሳይሆን ወይንም ህዝብን ለመግደል አፈሙዙን የሚያነሳ ሳይሆን ህዝብን ለመጠበቅ የሚቆም ሃይል የሚሆንባት፥ ሁሉም ዜጋ በሃገሩ ላይ ሰርቶ የሚያድግባት፥ተማሪው ተምሮ ያለአድልዎ ስራ የሚያገኝባት፥ ሰው ፍርድ ቤት ቆሞ ትክክለኛውን ፍርድ የሚበየንባት፥ ሰው ከሃገሩ ለነፍሱ ፍራቻ ወደሌላ ሃገር የማይሰደድባት፥ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ያልሆነባት ወዘተ።።።ሃገር ለመመስረት የሚያስችል መንገድ የሚፈጠር መስሎን ነበር አንጂ የቀድሞው የመለስ የጭቆና ዘመን ሳይቀየር የሚቀጥልባት፥ የወያኔን የቀድሞውን አላማውን የሚያስቀጥል ሎሌ ይሆናል ብለን ኣልነበረም። ነገር ግን አምላክ ከጎኗ ስለሆነና ኢትዮጵያ የጀግና ደሃ ስላይደለች የቁርጥ ቀን ልጆቿ በዘር ሳንከፋፈል ተረባርበን ከአጠላባት አደጋ መታደግ የዜግነት ግዴታችን ነው፥፥ ሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆቿን ኑ ትላለች፥፥ ኑ በተግባር ልያችሁ እያለች ትጮሃለች፥፥ ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኽ እንዳይሆንብን በኣቢይ ኣህመድ ኣደንዛዥ ቱልቱላ ሳንሽወድ ሃገራችንን ከወያኔና ኦነግ ኣሻጥር ብንታደጋት መልካም ነው።

 4. Dear Dagmawi Gudu Kassa,

  The politics of dummy emotion and the history of falsehood will not have place in the future of the Ethiopian political landscapes. The times of the political ideologies of the Debteraists are already over. No more room for nonsense assertion and empty noises.

  You are a subhuman and mentally retarded ane handicapped person. Your usual empty AKAKI SEREF will bring you the final nightmare to you and those like you! Watch out! Before you open your filthy mouth try to settle first your political problems with the Agewo, Qimanti and many others within the regional state of Amahara.

  The main problem is your mentality and the culture in which you grew up. The mentality and the culture of the dark era of Minilik, Haile Selassie and Derg which are still influencing and confusing you. You need redemption. But it is better if you reconcile yourself with the reality of this time. You cannot turn back the wheel of history. The empty akakii zeref will not help you. The ghost of Minilik also cannot help you. It is better if you accept the realities of your time and work on the democratic principles so that you will embrace with dignity and respect the future multinational democratic Ethiopia without suffering under inferiority complex. Don’t forget also you and your ancestors having been suffering a lot as Gojames and Gonderes under those inhuma systems of that empire state. From those systems you have inherited only pseudo prides, bad mentality and cultures under which you are still in custody. I wish that you will become free from that mentality as a good cultured human being.

 5. ውይ በሞትኩት እኔ ሰው አገኘሁ ብዬ ማውራቴ ነበር። የገማና የገለማ ጭንቅላትና አስተሳሰብ ያለህ የሆድህ ባርያ መሆንህን ሳላውቅ ወርቃማ ጊዜየን በከንቱ አባከንኩ – አሁን ሳይቀር:: በል ከነ ድንቁርናህ ደህና እደር:: ሰው ስትሆን ያገናኝን የኔ ገልቱ:: እ/ር ቢወቀስ ኖሮ አንተን እንዲህ አጃጅሎ በመፍጠሩ አሁን ነበር መውቀስ::

 6. “የቁርጥ ቀን ልጆቿ በዘር ሳንከፋፈል ተረባርበን ከአጠላባት አደጋ መታደግ የዜግነት ግዴታችን ነው!” ይላል ወያኔው Mootummaa ! የአጠላባት አደጋ የምትለው የትኛውን ነው? የአምሃራ ወይም የትግሬ የበላይነት ቀርቶ እዉነተኛ ፈደራሊዝም ቢሰፍን አደጋዉ ላሰባችሁት ኢትዮጵያን መልሶ የአምሃራ ምርኮ ለማድረጉ ካልሆነ በቀር ለማን? ለምን ነው?

  ምነው የነፍጠኛ ልጆች በሞላ ተንጫጫችሁሳ!? ምድረ ኢንተርነቱን በህልማችሁ ብትስሉት፣ መሬት ላይ ያለዉን እዉነታ የፋቃችሁ መሰላችሁ? ከደርግ | ፊዉዳል ዘመን ናፋቂዎች በቀር ወደ ድሮው ስርዐት ለመመለስ የሚያስብ ዬት አለ? ፈደራሊዝሙን እናፍረሰው እንኳ ቢባል እያንዳንዱ ፈደራል ስቴት በገዛ ፈቃዱ / በህዝብ ምርጫ ማጽደቅ አለበት። ምናልባት ከአምሃራ ክልል ዉጪ (እሱም ምናልባት ነው) የራሱን አስተዳደር የሚያፈርስ ግን አይኖርም። የአሉት ክልሎች እኮ ጠቅላይ ግዛቶች፣ መሪዎቹም ጠቅላይ እንደራሴዎች አይደሉም እኮ በንጉስ አቢይ የሚታዘዙ! እንደንጉሱ ዘመን ከላይ የሚታዘዝልሽ ከመሰልሽ እያንዳንዱ ክልል አንቀጽ 39 መጥራት ይችላል! ስለፈደራሊዝም መሰረታዊ ጭብጥ ተማሩ እስቲ you feudalists!

 7. አባ ጫላ
  ከእማራ ትከሻ ውረድ:: ለኢትዮጵያዊነት ከማንም በላይ በመሪነት የሰሩት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ( ተፈሪ መኮንን ጉዲሳ) ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አያና ኦሮሞዎች ነበሩ:: ለሸዋ የበላይነት ጦር አዘምተው የጎንደሩን ራስ ጉግሳ ወሌን ያስገደሉ ፊታውራሪ ሀበተጊዮርጊስ ዲነግዴ መሆናቸውን ታውቃለህ? ሀብተጊዮርጊስ የሸዋ ኦሮሞ ነበሩ:: የኢትዮጵያ የገዢው መደብ ብሄር አይለይም:: የአንድነት ሀይሎች አማሮች ብቻ አልነበሩም::ስለዚህ ይህ የአማራ ህዝብ ዘለፋህን አስተካክል:: እጅግ ብዙ ሚሊዮን አማራ በኦሮሚያ ኖሯል ወደፊትም ይኖራል:: ይህን ህዝብ ገፍታችሁ ገፍታችሁ እንዳትቀሰቅሱት:: ሌላው ማወቅ ያለባችሁ ዲጂታል ወያኔዎች fake Amhara በመሆን አዲስ የጦርነት አሰላለፍ ቀይሰዋል::

  Gamaada
  ጉዱ ካሳ ጨዋ የሆነ ውይይት ነው ያካሄደው:: አንተ የወረደ መልስ መስጠትህ የሀሳብ ድርቀት እንዳለህ ያስረዳል:: በዚህ ዘመን በስድብ ምንም የምታራምደው ነገር የለም:: በአማርኛ የፃፍኩትን አስተርጉም::

 8. There are backward individuals who can never learn and change themselves with the time. They are mentally still live in the 18th century. They cannot grasp what is going on allover Ethiopia. Insulting here and there is their hobbies. They can keep on their stupidity. But the emancipation of the Kimanti, Agawo, Sidama, Gamo, Waliyta and other peoples is inevitable. These peoples will celebrate soon their cultural and ideological independence from the past misdeeds.

  The Ethiopian peoples have been exploited  its natural and human resources in the last 150 years because of such cheap and self centered politics and policies. The social, political, cultural and economic developments of the people are extremely retarded by such backward and inhuman mentalities. Such individuals and their ruling systems  are parasites like a tapeworm which dehydrates its host continuously. 

 9. @አባጫላ፣
  ሜ ዋን ሲጋፋ’ዳ፣ ፣፣ ናሚቺ ኢንግሊፋን አካናቲ ዖሮሙማፍ ፋልሙ ፋካቴ ጋማፍ ጋማና ኩሩጲሱ ቱኒ ናሙም ኬኛ ሲቲፋካታ? አኒ ናቲንቶሌ ፎሊን ጋማዳ፣፣ ዋሩማ ቢኔንቲ ናቲፋካታ፣፣ አማ ናሚቻ “አባራጂ” ታና አካናቲ ሰልጲሱን ማልጄ’ዳማ? አካሲቲ ዖሮሙማፍ ፋልሙን? ሜቁማፋና ፋልሚኔ ዋዬኬኛ ቤክሲሳናሬ? ዮ ናሙምኬኛ ታኤ፣ አያኒ ዖሮሞ ቃልቢሳቲ ኢሳዴቢሱካ፣፣ ኬሲኮ አኩማ አቢዳቲ ጉባታ ማቃዖሮሞቲን አካንታኔ ኦጋቡኬሳሙ፣፣ ዮ ጃሪቲ ታኤ መንጉዶ ኬሳ ገሌ ዱቢ ቤኬ ቦርጩ ታናን አያኒ ዖሮሞ አካማሌ ኢሳቄራኡ፣፣

 10. Abba Wirtu,

  Waa’ee nama kami akka ati hassaa jirtuu anaaf hin galee? Ati garuu yoo dhugumaatti Oromoodha tattee qubee afaan Oromoof hin tanneetti maliif fayyaadamta? Qubee afaan Oromoo barrachuuf rakkoo qabida yoo taa’ee, olaa kee gaaffaachuu.

 11. አባን ራጂ ጉማ ኤኙሬ ጉዱካሳ ለሜሶ መሌ? አማኑማ ዖሮሙማንኬ? ኦዶታቴ ዳፌሲጋላ ቱሬ:)፣ኦፊ ማሉማፍ ቁላ’ዳብ’ዴ አካናቲ አራብሲታን?፣ ዋኑምፌቴ ቃልቢዳን ሚልኬቹ ሂንዳንዴቹ? አራብሱማ ታናፍ ማቃባሱታና ማሉማቱ ፊዴ? ባዬን ሲቲጋዳ ዱጉማፍ ዮ ዖሮሙማ ቃባቴፍ፣፣ አባጫላኒሬ ቃባናኤራፋኒ፣ ማሌ ኢኒስ ታካታካ አኩምኬ ኢሳቡታ፣፣ አኒ ዖሮሞ’ዱማ ተኤ ‘ዳላቴ አራብሶስ ካንቤኩፋና ሂንጉዳኔፋኒ፣፣ ሜ ኢቲያዲሜ፣፣ ቁቤታና ባራቹዳፍ ሂንባርባኔፋኒ ማሌ አፋን ኩ’ዳናን ዖዴሳ፣፣ ዳባሊቲሞ ናምኑምቲ ታና ቤኩ ኦላ’ዲሲ ቢያቱ ሂንጂሩ፣፣ ሲንሳዴፋ’ዳሞ፣ አማሪፋቲን ዖሮሚፋ ባሬሱን አናፍ ጃላላ፣፣ ማሊፍ? አናፍ አማሪፋን ኮባቲ ካን ዋራ አማራቲ ኦዶ ሂንታኢን ካን ሁንዳኬኛ ጄ’ዴታኒን አማ ዮና ጂራ’ዴፋኒ፣፣ አማን ዱኡቱ ሲንቁቤሱ፣፣ ኩን ዖሮሞ ማሌ ካንቢራ ናጎናን
  ኦፊ ኢልሞናማ ታኡንኮ ናጋአ፣፣ አማኑማ፣፣ ታኩማዩ ዋራ ወሩ ማሌ ኢጆሌን ቴኛ ዋዬ ቂማንቲፍ ወይጦ ኬሳ ጋልቴ ሂንቡኬሲቱ፣፣ ቁቤ ቤኩንኬ ዖሮሞ ሲጎናን ዋሪ ፋራንጂ ቁቤ’ዲሲቲ ጊኢዚ’ዳን ዋሪ ጢባርቱ ማል ኦፍሀጄቱሬ? ፎሊንኬ ናቲሂንቶሌ፣፣ ዋሩ ዋሩ ናቲአጆፍታፋኒ፣፣ ናጋቲ፣፣ ‘ዲፋማ ጉዳ ዮንዶጎንጎሬፍ፣፣.

 12. @ተሰማ
  “ከእማራ ትከሻ ውረድ” ላልከው ድሮም መች ወጣሁ? እንድ አንዳንድ የኢንተርነት ወንበዴዎች ህዝብን በጅምላ መዝለፍ አይቻለኝም፣ አድርጌም አላዉቅ። ነገር ግን ያለፈው 27 ዐመቱ የዎያኔ ዘመን የትግሬዎች አገዛዝ እንደነበረ ሁሉ፣ ያለፉት ከሚኒሊክ እስከ ደርግ ድረስ የአምሃራ ወይም በአምሃራ በላይነት ላይ የተመሰረቱ መንግስታት እንደሆኑ መካድ አይቻልም። በአምሃራ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ሲባል የአምሃራን ቋንቋ፣ ባህል እና ሃይማኖትን ማዕከሉ አድርጎ ሌሎችን ሲጨቁን የነበረ ማለት እንጂ አማራዎች ሁሉ ንጉሶች ወይም ጨቋኞች ነበሩ ለማለት አይደለም። የአምሃራ ሲስቴም (Amhara system) እስከሆነ ድረስ ደግሞ፣ ከሌሎች ብሄረሰቦችም ሰዎች ቢኖሩበትም ለሲስቴሙ የሚሰሩ እንጂ ለወጡበት ማህበረሰብ ስላልሆነ (they are coopted but do not represent the interest of their ethnics) የአምሃራ ሲስቴምነቱን አይቀይረዉም።
  አነታራኪው ያለፈው ታሪክ ሳይሆን፣ ካለፈው ተምረን ለወደፊቱ ምን ይበጃል ሲባል፣ በአምሃራ ስም መነገድ የለመዱ አሁንም ኢትዮጵያን ሊያፈራርሳት ሰበብ ወደነበረው አሃዳዊ ስርዐት እንመልሳት ብለው መነሳታቸው ነው። That is a no go area!
  እዚህ ላይ ስለ ሀይለስላሴ እና ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም ኦሮሞነት ወዲያ በለው (achi qabii, bishaan itti qabi! enyutu dhalchinaan?)። ኦሮሞነት (ወይም አማራነት፣ ሌላም) የደም ጉዳይ ብቻ አይደለም! ዋናው ሳይኮሎጂ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.