ም/ቤቱ ዛሬ በካሄደው ልዩ ስብሰባ የቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ምደባን ይፋ አደረገ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ የተዋቀሩት 10 ቋሚ ኮሚቴዎችን እንዲመሩ በተመደቡ ሊቀመናብርት ላይ በተናጠል ድምጽ በመስጠት ነው ስምንቱ እጩ ሊቀመናብርት በምክር ቤቱ ተቀባይነት ያገኙት፡፡

የሁለቱ ሊቀመናብርት ምደባ ግን ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል ፡፡

በዚህም መሰረት ስምንቱን ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲመሩ የተመረጡት፡-

1ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን

2 ለመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ መሀመድ ዩሱፍ

3 ለሰዉ ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ እምዬ ቢተዉ

4 ለሴቶች ወጣቶችና መህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ

5 ለተፈጥሮ ሀብት መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ

6 ለከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ አሸናፊ ጋኢሚ

7 ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ ጌታቸዉ መለሰ

8 ለግብርናና አርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ አልማዝ መሰለ ናቸዉ

በምክር ቤቱ ተቀባይነት ያላገኙት የሁለቱ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበሮች ደግሞ

1. ለውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ- አቶ ሞቱማ መቃሳ እና

2. ለገቢዎችና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ – አቶ አፅብሃ አረጋዊ ናቸው፡፡

በተሾመ መልዴ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.