ጎንደር ዙሪያ ገባው ከሰሞኑ! ከመተማ እስከ ነጋዴ ባህር ውጊያ ላይ ነው! ህወሃት ከሁመራ ጦር አዝምቷል!

/ር አብይ ጎንደር ገብተዋል!
====
የግጭቱ አነሳስ:-
ባለፈው ቅዳሜ እለት ነጋዴ ባህርን ዋና ከተማ በማድረግ አሁን አዲስ የተቋቋመው የምእራብ ጎንደር አስተዳደር የአዳኝ ሃገር ጫቆን ወረዳ ይመሰርታል። ከበአል አከባበር የሚመለሱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በቅማንት የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ስም የሚንቀሳቀሱ የህወሃት ቅጥረኛች ተኩስ ይከፈትባቸውና ቀሳውስትን ጨምሮ ወደ ስድስት ሰዎች ይገደላሉ።

#ሁለተኛ ኩነት:-
ቅጥረኛ ነፍስ አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ህዝቡ እና የአካባቢው የፀጥታ ሃይሎች አሰሳ ይገባሉ። ነገር ግን በከባድ እና በቡድን መሳሪያ የተደገፈ የአፀፋ ተኩስ ለሳምንት ያክል ገጥሟቸዋል። ይህን ማን አደረገው ለሚለው የማያሻማ ማስረጃዎች ተገኝተዋል።

#ሶስተኛ:- ከሁመራ 24ኛው ክፍለ ጦር ከተሰናባች ነባር የህወሃት ታጋዮች ጋር በመሆን በመተማ በኩል በመምጣት ከአካባቢው ማህበረሰብና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር ውጊው አሁንም እንደ ቀጠለ ነው። በተደረገው ውጊያ ከሞቱ እና ከተማረኩት ውስጥ ተሰናባች የህወሃት ታጋዮች የነበሩ እንዳሉበት ታውቋል። ውጊያውንም አስቸጋሪ ያደረገው እነዚህ ከ24ኛው ብርጌድ ከሁመራ የመጡት የሚዋጉት በመደበኛ ወታደር ደንብ ሳይሆን በጎሪላ ታክቲክ ዛፍ ላይ ሁሉ እየወጡ ነው። የአማራ ክልል የፀጥታ ሃይል ከ24ኛው ብርጌድ ከሁመራ ከመጣው ሃይል ጋር መግባባት ስላልቻሉ ፍጥጫው እንደ ቀጠለ ነው። ምናልባት ተንኮላቸውን ስለተረዱ ይሆናል በዛሬው እለት የቅማንት ማህበረሰብ በሚበዛበት አንድ አካባቢ ላይ ዛሬ ከሁመራ በመጣው ጦር ላይ ተኩስ ከፍተው ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።

#አራተኛ:-የአማራ ክልል አዲሱ የፀጥታ ጉዳይ ዋና ሹም የሆኑት ጀነራል አሳምነው ፅጌ በቀጥታ ህወሃት ብለው ባይጠሩትም የሰሞኑ ውጊያ በጎረቤት ክልል(ትግራይ) እና በጎረቤት ሃገር(ሱዳን ማለታቸው ነው) መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል።

#አምስተኛ:-በዛሬው እለት ሸህዲ ላይ በተካሄደው ከባድ ውጊያ የተሳተፉ የህዝብ ወገኖች ጦርነቱን በቀጥታ የከፈተብን ህወሃት መሆኑን በማያሻማ ማስረጃዎች አረጋግጠናል። እጅግ በተደራጁ ሁኔታ ስለገጠሙን ከቅርብም ከሩቅም ያለው የህዝባችን ወገን እንዲደርስልን በጥብቅ አሳውቁ ብለውናል።

#አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ነገ አርብ ጎንደር ስለሚገቡ ዶ/ር አብይ ለአቀባበሉ ቅድመ ዝግጅት ዛሬ ጎንደር ከተማ ገብተው ከህዝብ ከተውጣጡ ሰዎች ጋር በፀጥታ እና ተዛማች ጉዳዮች ውይይት ተደርጓል። የህወሃት የሰሞኑ የመተማ መስመር ጦርነት መክፈትም ይህን ጉብኝት ለማደናቀፍና ለማደብዘዝ የታለመ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። ይህን ተንኮል የተረዱ የጎንደር ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በመግባባት ለከተማዋ ፀጥታ ልዩ ትኩረት አድርገው በንቃት እየጠበቁ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።

#ማሳሰቢያ:-የሰሞኑም ሆነ የቆዩ የአካባቢው የፀጥታ መደፍረስ ስረ መሰረቱ ወያኔ መሆኑን ስንገልፅ ቆይተናል። ተዋልዶና ተዛምዶ በአንድ ወጥ ጎንደሬነት በኖረው በአማራውና በቅማንት ማሕበረሰብ መካከል ምንም ችግር የለም። ነገር ግን የወያኔን ከፋፍለህ ግዛው ልዩ ተልእኮ የተቀበሉ የቅማንት ማንነት ኮሚቴ ነን ባዮች ላይ ህዝባችን ከባድ ማስጠንቀቂያ እያስተላለፈባቸው ነው። ተጠናክሮ የመጣውን የወልቃይት ፍትሃዊ ጥያቄ ለማፈን ወያኔ እና ግብረ አበሮቹ የቅማንትን ካርድ በተደጋጋሚ ሲስቡ ከርመዋል። አሁን ግን የተንገሸገሸው ህዝብ በጋራ ወግዱ እያላቸው ነው።

#መደምደሚያ:-
የህወሃት ህልም በቅማንት ስም መተላለፊያ ኮሪደር በመጠቀም ከሁመራ ወደ ቤንሻንጉል መስመር ዘርግተው ታላቋን ትግራይ መመስረት ነው። ጎጃም መተከል የነበረውን አሁን ቤንሻንጉል ክልል ብለው በአማራው ላይ የማያባራ እልቂት የሚያቀነባብሩት ህወሃት መሆኑ ገሃድ የወጣ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከወልቃይት ራያ እና መተከል ድረስ የተደራረበው የህዝብ ብሶት ግን ይበልጥ መቀናጀት እየታየበት ስለሆነ የህወሃት የጥፋት እጆች መልሰው ላይሰሩ እየተቀረጠፉ ያልቃሉ። ለምሳሌም በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ ትግራይ የሚሄድ ስንቅ ካሁን በኋላ ክልክል ነው”በዳባት በኩል አይለመደኝም” ተብሎ ታውጇል። በሁመራ መስመርም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱ አይቀርም። ራያ በሩን ዘግቶ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው። ህወሃት የትግራይን ህዝብ መያዦ አድርጎ ከጎረቤቱ ጋር በር አዘግቶታል። መፍትሄው ያለ አግባብ በማናለብኝነት የተወሰዱትን ወልቃይትን፣ ሰቲት ሁመራን፣ ጠገዴን፣ ጠለምትን፣ ራያንና መተከልን ያለ ምንም ማንገራገር እና ቅድመ ሁኔታ ወደ ቀደመ ህጋዊ ይዞታቸው መመለስ ብቻ ነው።

ሙሉነህ ዮሃንስ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.