አማራውና ኦሮሞው ማነው? ሌላው ኢትዮጵያዊውስ ማን ሊባልና ሊሆን ይሆን?

አጭር ምላሹ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው:: ኢትዮጵያዊውን በሚናገረው ቋንቋ ኦሮሞ፣ አማራ፣ አኝዋክና ኑኤር፣ ሐረሪ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ ወ.ዘ.ተ እያልን በተለያየ ሥም የምንጠራው ያው ያንኑ ኢትዮጵያዊ ነው:: ሪቻርድ ፊይመን “የወፎችን ሥም ዓለም ላይ ባሉ ቋንቋዎች አውቀን ስንጨርስ ስለወፏ ሁሉንም አወቅን ማለት አይደለም። ቁምነገሩ ወፏን አተኩሮ ማስተዋልና ምን እንደምትሠራ ማወቅ ላይ ነው። በቅርቡ መረዳት የቻልኩት የአንድ ነገርን ሥምና ሥያሜና የዛን ነገር ምንነት ማወቅ የተለያዩ መሆናቸውን ነው” ይላል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በጎጠኞችና የጎሣ ፓለቲካ ምርኮኞችና ተከታይ መንጋዎች ጭንቅላት ውስጥ እንጂ ምድር ላይ ብሔር የሚባል ነገር የለም:: ብሔርም ዘር ወይም ጎሣ ያልሆነ የማህበረሰብ ስብስብ ነው:: ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመንን በዳበረ ኢኮኖሚ፤ የኢኮኖሚ መጣበቅና መቆራኘት (economic cohesion) የሚገለፁ ብሔሮች ናቸው:: እነዚህ ብሔሮች የተዋቀሩት በአረቡ፣ በጣሊያኑ፣ በእንግሊዙ፣ በፈረንሣዮች፣ በጀርመኑ፣ በፐርሺያው ወ.ዘ.ተ ውህድትና በታሪክ ሂደት በአንድ ቋንቋ የሚገለፅ ማህበራዊ ስብስብ ናቸው:: ዛሬ በኢትዮጵያ በብሔር ሥም ጠቅለንና ያለ ሥም አዲስ የዳቦ ሥም እየሰጠን የምንጠራቸው ለምሣሌ አማራ ትላንት ጎጃሜ፣ ወሎዬ፣ መንዜ፣ ቡልጋ፣ ተጉለቴ፣ ምንጃሬ፣ ጎንደር፣ አገው ወ.ዘ.ተ ናቸው:: ዛሬ ኦሮሞ የምንለው ኢጆሌ ባሌ፣ ወለጋ፣ አርሲ፣ ቆቱ፣ ኢሊባቡር ወ.ዘ.ተ ብለን እንጠራቸው የነበሩ ናቸው:: እነዚህ ሁሉ እንኳንስ የኢኮኖሚ መጣበቅና መቆራኘት (economic cohesion) ሊኖራቸው ቋንቋቸው በራሱ የተለያየ ዘዬ (Dialect) ያለው ነው:: ለምሣሌ በኦሮሚያ አምስት የቋንቋ ዘዬዎች ማለትም በምስራቅ ሐረርጌ በሰሜናዊ ባሌ የሚነገረው የቆቱ ዘዬ:፣ በደቡብ፣ በምዕራብ:፣ በሸዋ-አርሲና በወለጋ የተለያዩ ናቸው::
በኢትዮጵያ ውስጥ “የጎሣ ፌደራሊዝም” የተዋቀረው ቋንቋን እንጂ ዘርን መሠረት አድርጎ አይደለም:: ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን የቋንቋ እንጂ የዘር ልዩነት እንደሌላቸው የጎሣ ፓለቲካ መሃንዲሶቹ ጠንቅቀው በማወቃቸው ነው::

አንድ ቋንቋ በመናገር አንድ ሕዝብ ለመሆን ብቻውን በቂ ካልሆነ የተለያየ ቋንቋ መናገርም በብቻው የተለያየ ሕዝብ አያደርግም:: ልጆቻችን በምዕራቡ አለም ተወልደው በማደጋቸውና እንግሊዝኛን በመናገራቸው ወይም ጥቁር አሜሪካውያን በዝርያቸው እንግሊዛዊ ጭራሹኑ እይሆኑም:: ቋንቋ በመነካካት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላው ይፈልሣል (Contagious Diffusion):: ቋንቋ የሚገልፀው ተናጋሪውን ብቻ ነው:: ቋንቋ ማንነትን አይገልፅም:: ነገር ግን ሠዎች ሊካተቱ ኩሚፈልጉት ወይም ይገልፀኛል ለሚሉት ማንነትን ለመግለፅ ይረዳል::
ኢትዮጵያውያን ይብዛም ይነስ አንድ ሕዝብ ናቸው:: የተለያየ ቋንቋን ግን ይናገራሉ:: ይህ አንድ ሕዝብ አይደሉም ማለትም አይደለም::

ዛሬ ባሌውን፣ ወለጋውን፣ ሐረሩን፣ ከፋውን፣ አርሲውንና ኢሊባቡሩን ኦሮሞ ወይም ጎጃሜውን፣ ጎንደሬውን፣ ወሎዬውንና ሸዋውን አማራ ያደረገውና ኢትዮጵያዊነቱን ሊያስክደውና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነደፈው “የቋንቋ ፌደራሊዝምና የጎሣ ፓለቲካ” በለስ ቢቀናው የተለያየ የቋንቋ ዘዬ ያላቸውና በአካባቢ ስያሜ የሚጠሩት ወደ ትናንሽ ጎጦች መከፈላቸው አይቀሬ ነው:: የዛሬው የአማራ “ብሔር” ነገ ላይ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ እንዲሁም የዛሬው ኦሮሞ”ብሔር” የነገ ባሌ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቡር፣ ሐረርና ከፋ ተብሎ መከፈሉ አይቀሬ ነው:: አንዱ የሌላው ግለሰብና ቡድን አይወክለኝም ማለቱ ገሃድ ነው::
ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ብቻ ነን:: ብሔራዊ ማንነትን ወይም ሲቪክ ብሕረተኝነትን የንመርጠው ንስሃ ገብተንለት ሣይሆን የሚያስከትለውን ያልታሠሰና ያልታየን መዘዝ አሣምረን ስለምንረዳ ነው::
አይናችንን ከፍተን እውነትን እንመልከት። እውነት አርነትን ያወጣል። ደድብ ማለት እውነቱን እያወቀና እውነትን እያየ ውሸትን የሚያምን ነው::

ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ይለምልም!
ኢትዮጵያዊ ብቻ ነን!!
Hailu AT

Loading...

2 COMMENTS

  1. “አማራ ያደረገውና ኢትዮጵያዊነቱን ሊያስክደውና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነደፈው “የቋንቋ ፌደራሊዝምና የጎሣ ፓለቲካ”

    አትሳሳት አማራ ኢትዮጵያዊነቱን አይክድም::ከኢትዮጵያ ላለመገንጠል የሚታገል ብቸኛው አማራ ብቻ ነው:: ሌሎች የተመሰረቱት ለመገንጠል ሲሆን የሰነበቱት አክሳሪ ብቻ ስለሆነ ነው:; አማራን ለቀቅ እድርግና ሌሎችን ልክ ልካቸውን ግን ንገርልን

  2. “Kan qullaa dhaabatte irra, kan ibsaa ofitti qabde!” goes an Oromo proverb. Meaning: ራቁትዋን ከመቆምዋ: መብራት ወደ ራስዋ ማስጠጋትዋ ይባስ!
    “Gowwaan udaan irra taa’ee wallisa!” goes another. It means a fools sings while defecating.
    You exposed only your ignorance! Learn first before you try to teach!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.