ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በሰላም አዲስ አበባ ገብታለች

ወደፖለቲካ መግባት ሞትና እስር የሚጋብዝ አስፈሪ ድባብ በነበረበት ያ ጊዜ ግንባሯን ለግፈኞች የሰጠች የነፃነት ታጋይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የህግ ባለሙያዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል። በአሜሪካ ሲኖሩ የነበሩት የህግ ባለሙያዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ማለዳ ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ከሰባት ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ሀገር እንዲለመሱ ያነሳሳቸውን ነገር ሲናገሩም፥ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲያስችል ታልሞ የተፈጠረው ዕድል ነው።

አሁንም በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለፍትህ መስፈን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

ወይዘሪት ብርቱካን በፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፥ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስራች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል።

የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.