ጣና ሐይቅ በመንግሥትም በማኅበረሰቡም ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ሀብት ነው

‹‹ጣናንንም እንደ ሀሮማያ ሐይቅ አጥተነው ሐዘን እንዳንቀመጥ መጠበቅ ያስፈልጋል፤ ጣና እንደተፈጠረ ያለ፣ በስፋትና ውበቱ ልክ ቱሪዝሙን ለማሳደግ ትኩረት የተነፈገው ሐይቅ ነው፡፡›› ጎብኝዎች

ባሕር ዳር፡ጥቅምት 28/2011 ዓ.ም(አብመድ) በተለያዩ አምራች ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች ከሰሞኑ በባሕር ዳር ውይይት ላይ ነበሩ፡፡ ውይይቱን ያዘጋጀው ‹‹የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የፌዴራል ኤጀንሲ›› ሲሆን ኢንዳስትሪውን ለማሳደግ ባለሀብቶቹ በሚያነሷቸው ችግሮችና መፍትሔዎች ዙሪያ ለመምከር የተካሄደ ነበር፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎቹ ከመድረኩ በኋላ ጣና ሐይቅንና በውስጡ የሚገኙ ገዳማትን በከፊል ጎብኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዋ ዲዛይነር ትዕግስት ሰይፉ ጣና ሐይቅንና ገዳማቱን ከጎበኙት መካከል አንዷ ናት፡፡ ‹‹ክልሉ ቅርሶቹን የማስተዋወቅ ሥራ ላይ መጠንከር አለበት፤ ጣና በውስጡ በርካታ ሀብት የያዘ የክልሉ ብቻ ሳይሆን የሀገር ሀብት ጭምር መሆኑን ተመልክቻለሁ፡፡ ስለሆነም በመንግሥትም በማኅበረሰቡም ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ሀብት ነው›› ብለዋ ዲዛይነር ትዕግስት፡፡

ከጅማ የመጡት አቶ ንጋቱ ጡቄ ደግሞ ‹‹ባሕር ዳር በጣናና ዓባይ የታደለች ውብና ማራኪ ከተማ ነች፡፡ ‹ጣና ለዓባይ መንገዱ እንጅ መነሻው አይደለም› ሲባል የሰማሁትን በአካል ተገኝቼ በመጎብኘቴ ተደስቻለሁ›› ብለዋል፡፡

በጣና ሐይቅ ከሚገኙ ገዳማት መካከል እንደ ዘጌ፣ ክብራን ገብርኤል እና ደብረ ማሪያም የመሳሰሉ ገዳማትን መጎብኘታቸውን የገለጹት አቶ ንጋቱ ‹‹እነዚህን የተፈጥሮ ፀጋዎች እና መንፈሳዊ እና ሀብቶችና ቅርሶች መንከባከብ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡

በጣናና በዙሪያው የሚገኙ ቅርሶችን በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ሀገሪቱ ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንድታገኝ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በሰፊው መሥራት እንዳለባቸውም አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ጣና እንደተፈጠረ ያለ በስፋትና ውበቱ ልክ ቱሪዝሙን ለማሳደግ ትኩረት የተነፈገው ሐይቅ ነው፡፡ ለማልማትና ከሐይቁና ከዙሪያው ለመጠቀም አልተሠራም›› ብለዋል አቶ ንጋቱ፡፡

እንደ ሀሮማያ ሐይቅ ጣናንንም አጥተነው ሐዘን እንዳንቀመጥ በሚል ያሳሰቡት ጎብኝዎቹ ‹‹ጣና ውበቱን እና ቅርስነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የተደቀኑበትን እንደ እንደቦጭ የመሰሉ አደጋዎች ማስወገድ ይገባል›› ብለዋል አቶ ንጋቱ፡፡

በዳግማዊ ተሠራ/የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.