በአሜሪካ መንግስት የሚደገፍ ለ5 ዓመታት የሚተገበር የንባብ ባሕልን ማጎልበት የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ይደረጋል

በመላ ሀገሪቱ ለ5 ዓመታት የሚተገበር የንባብ ባሕልን ማጎልበት የሚያስችል መርሃ ግብር ነገ ይፋ ይደረጋል፡፡
• መርሃግብሩ 90 ሚሊየን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ይደረግበታል፡፡
ባሕር ዳር፡ጥቅምት 28/2011 ዓ.ም(አብመድ) የንባብ ክሂልን ለማጎልበት ታስቦ ይፋ የሚደረገው መርሃ ግብር በአሜሪካ መንግስት የሚደገፍ ነው፡፡

15 ሚሊየን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን የንባብ አቅም ማጎልበት ያስችላል መርሀግብሩ፡፡

በስራው ትኩረት የሚደረገውም የተማሪዎቹን የአፍ መፍቻ ቋንቋ ንባብ አቅም ማጎልበቻ ላይ ነው፡፡

ሀገራዊ መርሀግብሩ ነገ በሰሜን ሽዋ ዞን ይፋ ይደረጋል፡፡መርሃግብሩ 90 ሚሊየን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ይደረግበታል፡፡

ነገ በሰሜን ሽዋ ይፋ ሲደረግም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ፣የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላየ ጌቴ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ፡-አስማማው በቀለ

የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.