በምዕራብ ጎንደር ግጭት ነዋሪዎች ተፈናቀሉ 

በግጭቱ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ በመተማ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ዜጎች ከከተማዋ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ገላባት መግባታቸውን ተመልክቶአ፡፡ የቅማንት ብሔረሰብ አባላትም የግጭቱ ሰለባ እንደሆኑ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡

ትላንት ጥቅምት 26 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ዮሐንስ ከተማ ተፈጥሮ በነበረ ግጭት በርከት ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎች መጎዳታቸው እና ንብረታቸው መውደሙን ነዋሪዎች ለDW ገለፁ፡፡ በግጭቱ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ በመተማ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ዜጎች ከከተማዋ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ገላባት መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ  ተፈናቃይ “ጥቃት ያደረሱብን አካላት ከከተማዋ ውጭ የመጡ፣ በጎበዝ አለቆች የሚመሩ ናቸው” ብለዋል።  ከመተማ ሸሽተው ሱዳን ገላባት ከሚገኙ ሰዎች መካከል ከ15 ዓመት በላይ በከተማዋ የኖሩ ዜጎች ይገኙበታል ተብሏል። የቅማንት ብሔረሰብ አባላትም የግጭቱ ሰለባ እንደሆኑ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ አድነው አያናው በተከሰተው ችግር የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን በመግለፅ በአሁኑ ሰዓት የመረጋጋት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባዉን የመቀሌዉ ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሤ ልኮልናል።

 

DW
ሚሊዮን ኃይለስላሤ
አዜብ ታደሰ
ተስፋለም ወልደየስ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.