አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ምን እየሆነ ነው? (ሰርፀ ደስታ)

እንደምታዘበው ነገሮች ሁሉ በስሜትና በውሸት እንጂ ጽኑ መሠረት ላይ የቆመ ነገር አልታየኝም፡፡ እንደእውነቱ በዛ ቀውጢ ወቅት እንኳን ወያኔ እንደሚወድቅ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ለዛ ደግሞ ጽኑ እምነት እንዲኖረኝ ያደረገው ለዘመናት ሴረኞቹ አማራና ኦሮሞን እርስ በእርስ እንደጠላት እንዲሆኑ በማድረግ ለዘመናት ሲነጩባት የነበረችው አገር የእነዚህ ሁለት ትልልቅ ሕዝብ ግንኙነት በይፋ እያንሰራራ መምጣቱን አይቼ ነበር፡፡ የጉዳዩን ሚስጢር አውቀዋለሁ፡፡ ግን ማን ያስተውላል፡፡ እነ አብይና ለማ የሕዝቦችን መቀራረብ በመጠናከር ጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ሲገባቸው ተመልሰው ወሮበሎቹን እንለማመጣለን በሚል የሄዱበት አካሄድ ዛሬ ኢትዮጵያን ለአደጋ የዳረጋት ይመስላል፡፡ በግልጽ ኦነግና ወያኔ ላለፉት 27 ዓመት አብረው ሲሰሩ እንደነበር እያወቅን ልክ ኦነግ ከወያኔ ጋር ጠላት እንደነበር ሊነግሩንና ሊያስረዱን ብዙ ደከሙ፡፡ ኦነግ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሕዝብን በተለይም ደግሞ የኦሮሞን ሕዝብ  እየነገዱበት ያሉ ኦሮሞ ነን የሚሉ የወያኔ ቁልፍ ሰዎች እንዳሉ ብዙ ጊዜ ተናግረን ነበር፡፡ ወያኔ መሠረቷ ሲናጋና ስትንኮታኮት እብድ የሆኑት እነዚሁ ኦሮሞ ነን የሚሉ የወያኔ ቅልቦች ናቸው፡፡ እንግዲህ ማስተዋል ከሌላ ምን ማረግ ይቻላል?

ዛሬ ላይ አማራ ነን በሚል የተነሳ ሌላ ነጋዴ አለ፡፡ ሕዝብን የንግድ ዕቃ በማድረግ መበልጸግ እንደሚቻል ወያኔ ለብዙ ወሮበሎች ስላስተማረች ሁሉም ይችንው የስራ ዘርፍ ላይ ነው ትኩረቱ፡፡ አስተውሉ ብንልም የሚያስተውል ጠፋ፡፡ የቀደሙት መሪዎችን እጅግ በማጥላላት የወሮበሎች መፈንጫ የሆነች ምድርን ፈጥረናል፡፡ ብዙ ትንታኔዎችን ሳይ ትዝብቴ ብዙ ነው፡፡ መጀመሪያ በግልጽ አማራ ጨቋኝ ነው የሚለው ፖለቲካ አሁን አሁን ደግሞ የሥርዓት በገዥዎች የደረሰ ጭቆና እንጂ ሕዝብ እንደሕዝብ ጨቋኝ አደለም የሚል መደለያ ቢጤ እሰማለሁ፡፡ አባባሉ ትክክል ነው፡፡ የቀደሙት መሪዎች ጨቋኝ ለመሆናቸው ግን ለመናገር የሙራል ልዕልናው ያለን አይመስለኝም፡፡ የቀደሙት መሪዎች በእርግጥም አገር የመምራት መንፈስና ብቃት ነበራቸው፡፡ እንደ እውነቱም አንዱን ሕዝብ ከሌላው ሳይለዩ መርተዋል!! ይሄ ነው ግልጽ ያለው እውነት፡፡ በተቃራኒው ሕዝብ ለሕዝብ ያለእነዚህ መሪዎች የማይተዋወቅና ወደ ዘረኝነት ያደላ አስተሳሰብ ያለው ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ለተፈጠረው የዘረኝነት ችግር ወሮበሎች መምራት መጀመራቸው ነው፡፡ ሕዝቡን አስተሳስረውት የነበሩትን መሪዎች ስናጣ ወሮበሎች የመሪዎችን ቦታ ያዙ፡፡ የሆነው እውነት ይሄ ነው፡፡ ሕዝብ ለሕዝብ በእምነትና፣ መሪዎችና ማሕበራዊ ግንኙነቶች ይተሳሰራል፡፡ እምነትና ማሕበራዊ ግንኙነት ያላቸውን ሚና ሳልንቅ በኢትዮጵያ እውነታ ግን ትልቅ ድርሻ የነበራቸው መሪዎች ነበሩ፡፡ የሕዝብ ለሕዝቡ ግንኙነት ያለመሪዎቹ ጥብቅ አደለም፡፡ መሪዎቹ ሕዝብን ለማስተጋበር ብዙ ጥረውም ሕዝብ ለሕዝብ ለመዋሀድ ብዙ ውሱንነት አለ፡፡ የዘረኝነት መንፈሱም ከዚሁ መነሻ ነው ዛሬ ወሮበሎቹ የሚጠቀሙበት፡፡ ዛሬ አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ በብዙዎቻችን በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቦታ ተንቀሳቅሶ የሚሠራው የጎራጌ ሕዝብ ከራሱ ማህበረሰብ ውጭ ጋብቻ እንኳን የመመስረት ውሱንነት አለበት፡፡ ሕዝብ ለሕዝብ በሌሎችም እንዲሁ የምናያቸው መሠረታዊ ክፍተቶች አሉ፡፡ እዚህ ላይ ሕዝብን ለመክሰስ አደለም ግን ያለ መሪ ሕዝብ ለሕዝብ በብዙ ወጎችና የእኔ በሚላቸው ነገሮች ከሌላው ጋር መዋሀድ እንዳላስቻሉት ለማሳየት እንጂ፡፡ የኢትዮጵያን ነገስታት ጥረት ስናይ ዋና ሕዝቡን ያዋሃዱት እነሱ ሆነው እናያገኛቸዋለን፡፡ ከአጼ ሚኒሊክ ብንጀምር በነገስታት ቤተሰብ የሚደረግ ጋብቻ በአብዛኛው ይደረግ የነበረው ከሌላ ሕዝብ ጋር ነበር፡፡ ለምሳሌ ሚኒሊክን ራሳቸውን ብንወስድ ከዋና አጋራቸው ከጎበና፣ ከራስ አሊ እና ከመሳሰሉት ጋር ነበር ልጆቻቸው ጋብቻ ያደረጉት፡፡  ዛሬ የእነዚያ ቤተሰብ ዘሮች በሕይወት ይኖራሉ በቅርቡ የኢያሱ የልጅልጅ የተባሉ ሰው ከጀርመን አገር ቤት ገብተው አይተናል፡፡

ወደ ኃይለስላሴ ስንመጣ ሌላ ሰፊ ጥረት እናያለን፡፡ ኃይለሥላሴ ዘር እምነት ሳይሉ ከጠርፍ ሳይቀር ያሉ የሕዝብ ልጆችን በማስተማር ለሕዝቦች ውሕደትና አገር መገንባት ትልቅ ሚና ሲጫወቱ ነበር፡፡ ያም ሆን በዛም ዘመን በአለአባት የተባሉ ከዛሬዎቹ ወሮበሎች የማይተናነሱ ስለነበሩ የኃይለስላሴን ምስል በተነገረን ሁኔታ እንድናየው ሆነ፡፡ እውነቱ ኃይለስላሴ በተለይ ትምህርትና አከርን ለማሳደግ ጥሩ ሀሳብ የነበራቸውን ግለሰቦች ዘር እምነት ሳይለዩ ትኩረት ሰጥተው ሲያበረታቱና ሲረዱ ነበር፡፡ የታዋቂው ነጋዴ የኢትዮጵያን አማልጋሜትድ ባለቤት የነበሩት(አሁን አማልጋሜትድ መኖሩን አንጃ) አቶ ገብረየስ ቤኛ ለአገርና ሕዝብ ጠቃሚ የሚሉትን ግን ለራሳቸው ንግድ የሚሆንን ሀሳብ ለንጉሱ አቅርበው ንጉሱ በግልጽ ከልዩ ዘር ተወለድኩ ከሚለኝ ከሥራ የተወለደ ይበልጥብኛልና በርታ ብለው ገብረየስን በኋላ ለደረሱበት አለምአቃዊ ትልቅነት ዋና አበረታቻቸውና በሚያስፈልጋቸውም ደጋፊ ኃይለሥላሴ ነበሩ፡፡ ሌሎችም ብዙ፡፡ ትምህርት በተመለከተ ከቦረናና ሌሎች ጠረፍ ቦታዎች ሳይቀር በአዳሪ ትምህርት ቤት እያስተማሩ ብዙዎችን ለብዙ ትልልቅ ቦታ አብቅተዋል፡፡ እንደ እውነቱ እነዚህ መሪዎች በዘር በእምነት ለይተው የጠቀሙት አልነበረም፡፡ ደርግ ብዙ ጥፋት የበዛበት ቢሆንም ግን በዘርና እምነት ለይቶ ያጠቃው ወይም የረዳው የለም፡፡ እንግዲህ መሪነት ከመሪዎች ወደ ወሮበሎች ስትመጣ ነው አሁን የምናየውን አይነት ሕዝብን ከሕዝብ በማለያየት የራስን እንጀራ መጋገር የተጀመረው፡፡ ከየትም የመጣ ወሮበላ መሪ ሊሆን አይችልም፡፡ የ60ዎቹ አብዮት አራማጅ የነበሩ ሕዝብና አገር ማለት የማይገባቸው ሥሜት የሚነዳቸው በማርክሲስትና ሌኒኒስት እምነት ባርነት ሥር የወደቁ በመሆናቸው ኢትዮጵያን ያለመሪ አስቀሯት፡፡ ለወሮበሎችም እንዲል እንዲያገኙ ሆነ፡፡

አሁን የማያቸው የአገሪቱ መሪዎች ግልጽ አደሉም፡፡ መሪነት ከልጅነት ጀምሮ በሚያድግ አስተሳሰብ እንጂ በትምህርትም በተነግሮም አይሆንም፡፡ የዓለም አገራትም ሁሉ የተከተሉት ይሄን ነው፡፡ የቀደሙ መሪዎችን ቢያንስ ለምልክት እስካሁንም ይዘው ይገኛሉ፡፡ ዛሬ በአደጉት አገሮች የምናያቸው ነገስታትና የነገስታት ቤተሰብ የሕዝብ ምልክትነት ሚና መሪነት መሠረት እንዳለው ለማሳየት ምልክት እንዲሆኑ ነው፡፡ እኛ ያጣነው ይሄ ነው፡፡ በመሆኑም ወሮበሎች መሪነቱን ያዙት፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ነገር እጅግ የሚያሰጋ ነው፡፡ ወሮበሎቹ በሰፊው በአገሪቱ እደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ሴራቸውን እየዶለቱ ነው፡፡ እንዲሁ እስከምርጫ ድረስ ቀጥለው በምርጫ ሰበብ ትልቅ ሁከት በአገሪቱ ለመፍጠር እየሰሩ ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በታች ዕድሜ የቀረው አገራዊ ምርጫ አገር ሳይስተካከል ከተደረገ አደጋው ብዙ ነው፡፡ ብዙ ችግር አለ፡፡ መሪ ነን የሚሉት ሕዝብን ከሕዝብ በደንብ መሠረት ይዞ ከማቀራረብ ይልቅ የተራ አስተሳሰቦች መፈንጫ አገር እንድትሆን ትልቅ ክፍተት ፈጥረዋል፡፡ ዛሬ ላይ ሕዝባዊ ጉባኤ እያደረጉ ያሉት አገሪቱን እንመራለን የሚሉት ሳይሆኑ ወሮበሎቹ ናቸው፡፡ በተለይ በኦሮሚያ እየሆነ ያለው በጣም ያሳዝናል፡፡ በአለፉት አመታት በምስራቅ በኩል በአብዲ ኢሌ ሲሳበብ ነበር፡፡ ከጅምሩም ኦነግ በዚህ የሕዝብ መፈናቀልና እልቂት እንዳለበት ስንናገር የሰማ የለም ዛሬ በምዕራብ እየሆነ ያለውንም እያዩ ሊያስተባብሉትና ምንም እንዳልተፈጠረ ሊያሳዩ ያስባሉ፡፡ እንግዲህ መሠረት የሌለው ሕዝብ እንዲህ በወሮበሎች ባርነት ሥር ወድቆ መከራው ይቀጥላል፡፡ ሚዲያዎች ስለመሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ለሕዝብ ከማሰራጨትና ሕዝብን ግንዛቤ ከማስጨበጥ የባለሥልጣናትና የአክቲቪስት ዲስኩር ሲግቱን ይውላሉ፡፡ ሰው ወደራሱ ተመልሶ እውን ምን እየሆነ ነው ብሎ ማሰብ እስካልቻለ አደጋው ብዙ ነው፡፡ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ሌላም መጥፊያ የሆነ ዘረኝነት እንጂ ክብርም ልዕልናም አደለም፡፡ ዘረኝነት ነው! መዋረድ ነው! የቀደሙ መሪዎች ይሄን ነበር ሲያክሙ የኖሩት! ኦሮሞ፣ አማራ ምናምን እያሉ በስሜት እያጋለቡት ወደ እራሳቸው ወጥመድ እየከተቱት ቋሚ የመከራ ባሪያ አድርገውት እነሱ ይኖሩበታል፡፡ ሁሉም ያስተውል! ቆይቶ ስለሚሆነው ይህን እናገራለሁ! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል!

አመሰግናለሁ!

ልዑል አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

Loading...

3 COMMENTS

 1. What you have warned us all here is not something to be taken lightly. I could not agree more. Ethiopia has fallen in the hands of hooligans for 27 years and counting. This up to no good, hooligans, took power in 1991, with no leadership experience, without the slightest fear of God, no education, only hatred, have run the country into a ditch. Sure, they staged sham elections for international consumption. Now they have ‘appointed’ or ‘anointed’ upon us a ‘shume’ (appointee) who was groomed by them and who seem to have no clue about the consequences of his ‘medemer’ philosophy. It is sad!

 2. ያለውን የፖለቲካ ሙቀት ብዙ ግዜ ጥሩ መለኪያ ነው ያለህ! እዛው ነዋሪ መሆን አለብህ!
  የማይገባኝ የመንግስት አድትዋጽኦ የህዥብን ደህንነት በማስከበር ምንድነው? ወይስ መንግስት የሚመለከተው የተወስኑ ዜጎችን ነው? ወይስ በአገሩ መንግስት የለም?

 3. “ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ሌላም መጥፊያ የሆነ ዘረኝነት እንጂ …” says a desperado ‘I-know-all’ demagogue called ሰርፀ ደስታ. He does not even know the difference between ‘ዘር’ and ‘ዘረኝነት’ and writes down his ignorance! To give emphasis to his falsehoods, he completes his every other sentence with something like “ይሄ ነው ግልጽ ያለው እውነት፡፡”! Shameless!

  “ኦነግ ከወያኔ ጋር ጠላት እንደነበር ሊነግሩንና ሊያስረዱን ብዙ ደከሙ፡፡” Yes, we did not know that you are incapable of understanding anything! Probably your brain is hard-wired!

  “Nothing in all the world is more dangerous than sincere ignorance and conscientious stupidity”!
  Martin Luther King, Jr.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.