ቻይና የመጀመሪያውን ተጣጣፊ ዘመናዊ ስልክ ሰራች

ለመያዝ ቀላል፣ ቢወድቁ የማይሰበሩ እና በአነስተኛ ወጭ የሚሰሩ ናቸዉ፡፡
ባሕር ዳር፡ጥቅምት 26/2011 ዓ.ም(አብመድ) ፍሌክስፓይ የሚል ስያሜ የተሰጠው ዘመናዊ ስልክ በቻይናው ሮይሊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምራች ኩባንያ ነዉ የተሰራው፡፡

20 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ሰሌዳ(ስክሪን) ሲኖረው ከሁለት እኩል መታጠፍ ይችላል፡፡ ስልኩ በሚታጠፍበት ጊዜ ከሁለት ጎን ካሉት ባሻገር ተጨማሪ ሶስተኛ ለስልክ ጥሪዎች እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል ሰሌዳ አለው፡፡ አጠቃላይ ክብደቱም 320 ግራም ብቻ ነው፡፡ ሁለት ጥራት ያላቸው ካሜራዎችም ተገጥመውለታል፡፡

ዘመናዊ ስልኩ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ለሁለት መታጠፍ የሚችል ቴክኖሎጂ ነዉ ተብሏል፡፡ የኩባንያዉ ዳይሬክተር ዶር. ሊዩ እንደተናገሩት ስልኩን ለመስራት ሶስት ዓመታትን ፈጅቷል ብለዋል፡፡

ታጣፊ ስልኮቹ ከሌሎች ደረቅ የመስታዎት ሰሌዳ ካላቸዉ ስልኮች ይልቅ ለመያዝ ቀላል፣ ቢወድቁ የማይሰበሩ እና በአነስተኛ ወጭ የሚሰሩ ናቸዉ ተብሏል፡፡ ይሁንና እስከ አንድ ሺህ አራት መቶ 52 ፓውንድ ወይም 51 ሺህ ብር አካባቢ ዋጋ ተተምኖላቸዋል፡፡

ሳምሰንግ እና ሁዋዌን የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎች ፈጠራውን ለመግዛት እና ለገብያ ለማቅረብ ጥረት መጀመራቸውን ዴይሊ ሜል አስነብቧል፡፡

በቢኒያም መስፍን
የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.