ኦነግና ወያኔ፡-ከመጀመሪያው ስንናገር ነበር ማን ይስማ! (ሰርፀ ደስታ)

ኦነግና ወያኔ ለዘመናት ሲቆምሩበት የነበረው የወያኔ መራሹ መንግስት ሲፍረከረክ የወያኔ የክት የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ምንም ሊገባው ያልቻለ ኦሮሞን እየገበረ ገንብ ሲከፈለው የነበረው ኦነግ አሁን ከወያኔም በላይ አብዷል፡፡ የሚያሳዝነው አሁንም የኦሮሞ ሕዝብ እየገባው አደለም፡፡ ዛሬ ኦነጋውያን ከወያኔ የሚሰፈርላቸው ቀለብ ስለቆመ ኦሮሞን ሁሉ አንቀሳቅሰው አሁን ለውጥ ያመጡትን ለመጣል የሞት ሽረት ትግል ላይ ናቸው፡፡ የሚከተሉትን አውነቶች ዳግመኛ እንድታስተውሉልኝ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ የነገሮች ተንታኝ(ሲቺዌሽን አናሊስት) እንጂ ነብይ አደለሁም፡፡ የምናገረው ከምንም ተነስቼ አደለም

 1. ወያኔ ሙሉ በሙሉ አቅም በነበራት ጊዜ ሁሉ ኦነጋውያን የሉም ሁሌም ወያኔ የሆነ ነገር ሲገጥማት ወደ ኦነግ መንደር ትሮጥ ነበር፡፡ ይሄ ቁማር አብዛኛው ኦሮሞ በኦነግ ሥም እየታረደ ኦነጋውያን ዋና የኑሮአቸው መሠረት ነበር
 2. ወያኔ መሠረቱ ሲናጋ ኦነጋውያን በየአለበት መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ብዙ ጥፋትም አደረሱ፡፡ በዋናነት ግን ኢላማ ያደረጉት አሁንም የኦሮሞን ሕዝብ ነው፡፡ ምክነያቱም ሕዝቡን በመንግስት ላይ ለማሳመጽ ሲባል ነው፡፡ በአብዲ ኢሌ ሽፋን በትልቁ የሱማሌ ኦሮሚያ ድንበር የሆነው የኦሮሞ እልቂትና ስደት የወያኔ፣ ኦነግና አብዲ ኢሌ የጋራ ጥምር ዘመቻ ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ኦነግ ሕዝብ በዛ አካባቢ ሰው እየገደለ መከላከያ አልረዳንም ብሎ እንዲያስብ ሕዝቡን እየቀሰቀሰም ነው፡፡ ኦኤምኤንም ይሄንን እያስተባበረ ነው፡፡
 3. የምስራቁና ሌሎች ቦታዎች ከሞላ ጎደል በቁጥጥር ስር ሲሆን ኦነጋውያን ፊታቸውን ወደ ምዕራብ አዞሩ አሁን በግልጽ ጦርነት እያወጁ ነው
 4. አዲስ አበባንና ቡራዩ የሆነውንም አስተውሉ ከጀምሩ ኦነግና ወያኔ አስበውበት ነበር ግን ያሰቡትን ያህል የተሳካ አልመሰለኝም፡፡ ይህ አጋጣሚ ብዙ ድብቅ የጥላቻና ዘረኝነት አመለካከት የነበራቸውን ሁሉ ይፋ አወጣ፡፡ አሁን ላይ ብዙዎቻችን እጅግ አዝነናል፡፡
 5. እነጀዋርና ቡድኑ ከወያኔና ወያኔ ደጋፊዎች ዳረጎት የሚቀበሉ ነበሩ፡፡ ከፈለጋችሁ ሁኔታዎችን የመመርመር አቅሙ ከአላችሁ በዚህ ቡድን ሲሰራጩ የነበሩ ወያኔን የሚቃወም በሚመስል ግን ለወያኔ ብዙ እገዛ ሲያደርጉ እንደነበር ትታዘባለችሁ፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ መፈረካከሱ እውን ሲሆን እነጀዋር በጣም ነበር የደነገጡት፡፡ አብይ ከኋላ ያለውን ማንነታቸውን ስለሚያውቅ እርምጃ ይወስዳል ብለው ፈርተው ነበርም፡፡ ሆኖም ከሚኒሶታው የአብይ ጉብኝት በኋላ ምን እንደተረዱ በአላውቅም ተረጋጉ፡፡ መረጋጋትም ብቻ አደለም እንደውም በአብይ መንግስት ደጋፊነት ሴራቸውን በሰፊው እያሰራጩ ነው፡፡ ጀዋር አገር ቤት በተንቀሳቀሰባቸው ቦታዎች አሮሞን ለቀጣይ ገበያ እያዘጋጀ ነበር፡፡ በሀረር የውሀ መቋጥ የእሱ ምክር ነበር፡፡ በአዲስ አበባም ተመሳሳይ ሽብር ሲዶለት ነበር፡፡ ይሄን ሕዝብ እንዲያውቀው፡፡
 6. በአጠቃላይ ሕዝብና አገር ሠላም ከሆነ እነዚህ ቡድኖች ወንጀላቸው እንደሚጋለጥ አሳምረው ስለሚያውቁት ያላቸው አማራጭ አሁን የመረጡት ብቻ ነው፡፡

ይሄን ሊንክ እዩት ኦነጋውያን እየፎከሩ ነው https://www.facebook.com/kuushmedia/videos/499044100573030/

እኔ ግን እላለሁ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ደግሞ ለኦሮሞ ሕዝብ የማንም አረመኔ ወሮበላ የንግድ እቃ መሆን ይብቃ፡፡ ንቃ! እየሆነ ያለው ይሄ ነው፡፡ ከአስተዋላችሁ በአለፉት 27 ዓመታት ወለጋና አርሲ ብዙ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች የተፈጠሩበት ነው፡፡ ይሄን ስል ኦሮሞን ለመከፋፈል ይሉሀል፡፡ ለማንኛውም ሕዝቤ ሆይ የሚያዋጣህን አስብ፡፡ የወሮበሎች የሞት እራት አትሁን፡፡ የእስከዛሬው በቢቃ ጥሩ ነው፡፡ ወሮበላዎችን መንግስት እርምጃ መውሰድ ቢችል ጥሩ ነበር ግን ምን አዚም እንደያዘው እኔንም አልገባኝም፡፡ የአማራ ሕዝብ ቢጠነቀቅ ጥሩ ነው፡፡ በዚህ አካሄድ ለሚቀጥለው 10 ዓመት ብዙ ኦሮሞዎች በጥላቻና ዘረኝነት ልክፍት ተበክለው ይሄው ኦሮሞንም መላ አከሪቱንም ሠላም እንደነሱ እንዲሁ ያለ ማህበረሰብ አማራ ውስጥ ይፈጠራል፡፡ አሁንም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ ሰውን በድንጋይ ወግሮ መግደል ሕዝባችን እየተለማመደው ያለ አረመኔነት ነው፡፡ ሌሎችን ማቀፍ መልካም ነው፡፡ በዚህ ላይ በአማራ ክልል ሰሞኑን የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችና መልዕክታቸው መልካም ነው ከሞላ ጎደል፡፡  ጌታቸው ረዳ ጥሩ መልዕክት ነው የሰጠው፡፡ ሕዝብ በደንብ ተረድቷል፡፡ ከዚህ በፊትም ይሄ ሰው ነበር ለወሮበሎች መውደቅ ትልቁን ሚና የተጫወተው፡፡ የሰውዬው ስሜተኝነት የወያኔን ሴራ ሕዝብ እንዲረዳ ትልቅ ሚና አለው፡፡ የራያና የወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡ እንጂ ሕገ-መንግስት የሚባለው የመለስና የኦነጋውያን የጥንቆላ ትብታብ አደለም የሚፈታው፡፡ ይሄን ሕገ-መንግስት የሚሉትን የጥንቆላ ሰነዳቸውን ባያነሱት ጥሩ ነው፡፡ አገሪቱ መሠረታዊ ሕጎች አሏት፡፡ ፌደራሊሙ በተወሰነ ማሻሻል እንደድሮው በክፍለሀገር ቢደራጅ መልካም ነው፡፡ ያኔ ወለጋና አርሲ በኦሮሞነት ስም እየፈነጩበት ያለው ኦሮሚያም ሐረርም በሀረሮች፣ ባሌም በባሌዎች ኢሊአባቦራም ቦረናም በየራሳቸው ይተዳደራሉ፡፡ በወያኔ ሲተዳደር የነበረው የአማራ ክልልም እንዲሁ፡፡ ኦሮሞ ያ በሬዱ ጂማ ማለቱን ትቶ ያ በሬዱ ኦሮሞ ማለት ሲጀምር ነበር የወደቀው፡፡ ዛሬ አማራ ነኝ የሚል ዘፈን ስትሰቡም የውድቀት ምልክት እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ወሎዬዋ፣ ጎጃሜዋ፣ ምናምን እንዳልተባለ ብዙውን ባሕልና ማሕበረሰብ በአንድ አማራነት ማጨቅ አደጋውን ቆይታችሁ ታዩታላችሁ፡፡ በእኔ እምነት ሶማሌ አፋርና ጋምቤላ በተወሰነ በክልልነት ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡ አማራና ኦሮሚያ ግን እያንዳንዳቸው ቢያንስ 3 ቦታ መበተን አለባቸው፡፡ ትግራይ ወደነበረበት ወደ ተከዜ ማዶ መሰብሰብ አለበት፡፡ አዋሳኝ ቦታዎች ለሕበረብሔርነት በተለያየ ቋንቋ እያንዳንዳቸው በክልል ቢቋቋሙ፡፡ ለምሳሌ ሸዋ ከብዙ ነገሩ አንጻር እራሱን የቻለ ክልል ሆኖ ቢዋቀር፡፡ ሸዋ ማለት የድሮው ሸዋ እንዳለ ማለት ነው፡፡ ቦረናና ሱማሌ አዋሳኝ ቦታዎች ከሁለቱም የተውጣጣ ክልል ቢኖራቸው፡፡ የጋራ ክልል ሲኖር ለድብንበር መጣላቱ ይቆማል፡፡ በአጠቃላይ ከ16-20 የሚሆኑ ክፍለአገራት ይኖራ፡፡ ይሄን የሚቃወሙት በጅምላ ማንነት ውስጥ ተደብቀው በሕዝብ የሚነግዱ እንደሆኑ አስተውሉ፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው! ቅዱስ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ማስተዋልንና በረከትን ይስጥ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

3 COMMENTS

 1. “በእኔ እምነት ሶማሌ አፋርና ጋምቤላ በተወሰነ በክልልነት ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡ አማራና ኦሮሚያ ግን እያንዳንዳቸው ቢያንስ 3 ቦታ መበተን አለባቸው፡፡ ትግራይ ወደነበረበት ወደ ተከዜ ማዶ መሰብሰብ አለበት፡፡ አዋሳኝ ቦታዎች ለሕበረብሔርነት በተለያየ ቋንቋ እያንዳንዳቸው በክልል ቢቋቋሙ፡፡ ለምሳሌ ሸዋ ከብዙ ነገሩ አንጻር እራሱን የቻለ ክልል ሆኖ ቢዋቀር፡፡ ሸዋ ማለት የድሮው ሸዋ እንዳለ ማለት ነው፡፡ ቦረናና ሱማሌ አዋሳኝ ቦታዎች ከሁለቱም የተውጣጣ ክልል ቢኖራቸው፡፡ የጋራ ክልል ሲኖር ለድብንበር መጣላቱ ይቆማል፡፡ በአጠቃላይ ከ16-20 የሚሆኑ ክፍለአገራት ይኖራ፡፡ ይሄን የሚቃወሙት በጅምላ ማንነት ውስጥ ተደብቀው በሕዝብ የሚነግዱ እንደሆኑ አስተውሉ፡፡” Your idea is a sensible and practical one if only people would listen. That said, though, with the way things are, rapidly changing, I don’t think ‘Amhara’ has left with any good option except organizing itself. Yet, I subscribe to your idea that this ‘Amhara sibseb’ should have the ultimate objective of throwing away the EPRDF yoke all together and usher the return of Ethiopia with the old administrative provinces with a federal structure.

 2. Save your chrocodile tears, Weslatta! Leave Oromo matters to Oromos. You are dreaming of your parents Xeqlay Gizat and Gasha Meret. That will never come again!

 3. በጣም ያሳዝናል ፡፡ እኔ እነኢብሳ ኢትዮጵያ ሲገቡ ንግግራቸው እውነት መስሎኝ ቀልቤን ስቦኝ፣ ጆሮዬን ላበድራቸው ዝግጁ ነበርኩ፡፡ ይሄው ኦነግ ከገባ ጀምሮ ዜናውን አጣበው የያዙት ጸብና ግድያ ብቻ ነው፡፡ መንግሥት እስከመቼ እንደሚታገሳቸው አልገባኝም፡፡ በሽብር በግድያ ካላዋጣህና ካልሰራ ስልትን መቀየር አዋቂነት ነው፡፡እስከመቼ ህዝብ እንደሚጭርሱ አይገባኝም፡፡
  የሚገርመው ደግሞ በዓለም ደረጃ በሽብርተኛ ሥም ኦነግን አስመዝግቦ በየበረሃ እያሳደደ ያስገዳልቸው፣ ያንከራተታቸው የዛሬ ወዳጃቸው ወያኔ ነው፡፡ አሁን አብረን በአንድ ቂጥ ካልፈሳን የሚሉት ሽርጉዱማ ተነቆትባቸዋል;፡ አማራን ጢቢጢቢ ለመጫወት ነበር፡፡ አዳሜ ሞኝሽን ፈልጊ!

  ወያኔ አልሞት ባይ ተጋዳይ ናት ነገር ግን ኦነግ የተሰጠውን የዐብይን ጥሪ ተጠቅሞ ይሄ በየቦታው ወገኖቻችንን ማፈናቀል ትቶ፣ ህዝብ መጨረስ ትቶ በሰላም የፓለቲካ ለውጥ ማምጣቱ ይሻለው ነበር፡፡ እውነቱን ለመነጋገር ማንም ተቃዋሚነት አያሰማም እንጂ የዐብይ አስተዳደር ኦሮሞ በኦሮሞ ነው፡፡ ብልጥ ህፃን የሰጡትን እየበላ ያለቅሳል እንደሚባለው ወይ እስርቤት ወይ አውጥተን ሳንጥላቸው የተሰጣቸ ኦነግ የተሰጠውን እድል በአግባቡ መጠቀም ይሻላቸዋል፡፡ እድሜ ልክ አገር እያመሳቀሉ፣ የህዝብ ሰላም እየነሱ የሚታገሳቸው የለም!

  ያቀርብካቸው ሃሳቦች እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆንና ውጤቱን እጠራጠራለሁ፡፡አዬ አንተ ደግሞ የሸዋ ህዝብ ሳላሙን ፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉም በፊት፣ መጀመሪያ ግን ኦሮሞዎቹ በጣም የተክፋፈሉ ስለሆነ መጀመሪያ እርስ በእሳቸው ተቧቅሰው እስኪዋጣላቸው መጠበቅ አለብን፡፡ ከእራሳቸው ጥላ ጋር በስላም የመኖር አቅም ያላቸው አይመስለኝም፡፡ አንዱ ቢቸግረው ሃሳብ ሰጥቶ የጻፈውን ሳነብ ለኦነግ ጸበል አዞላቸዋል፡፡ lol

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.