‹‹አማራን ለማዳከም ከሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ፍላጎት የለንም፡፡›› አብን

‹‹የአማራ ብሄርተኝነት ኢትዮጵያዊነትን አያደበዝዝም፡፡ሀገር የምትመሰረተው በአንድ አካባቢ በሚፍጠር ጠንካራ የፖለቲካ አመራሮች ነው ፤የአማራ ብሄርተኝነትም ኢትዮጵያዊነትን አያደበዝዝም፡፡›› የአብን አመራሮች

ባሕር ዳር፡ጥቅምት 14/2011 ዓ.ም(አብመድ) አማራ የራሱ የሆነ ፊደል፣ታሪክ እና ቋንቋ እንዲሁም ብዙ የህዝብ ቁጥር ያለው ታላቅ ህዝብ ስለሆነ ስለ አማራነት ማውራት ስለ ኢትዮጵያዊነት ማውራት ነው ብለዋል አመራሮቹ፡፡

የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ የተደራጀ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲ አስፈላጊ ነው ያሉት የአብን አመራሮች አማራን ለማዳከም ከሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግን ለመስራት ፍላጎት የለንም ብለዋል፡፡

ከአብን ከፍተኛ አመራሮች መካከል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ ፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መልካሙ ሹምዮ ፣የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት አብን የህዝብ ብሶት የወለደው ድርጅት ነው፤ በመሆኑም ድርጅቱ ትግሉ ዳር እስኪደርስ ድረስ የአማራን ህዝብ በማታገል ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

የአዴፓ አመራሮች ከዚህ በፊት ለመወያያ የሚሆን አዳራሽ ለመፍቀድ ፍላጎት እንዳልነበራቸው አውስተው አሁን ላይ ግን የድርጅቱን ዓላማ በመገንዘብ የነበራቸውን አቋም ቀይረዋል ብለዋል፡፡

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ለአብን እየሰጠ ያለው የዘገባ ሽፋን አነስተኛ ነው ያሉት አመራሮቹ ድርጅቱ ለአብን የሚሰጠውን የአየር ሽፋን ከፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-አዳሙ ሽባባው / የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.