አብን የትግራይ ክልላዊ መንግስት በራያ አማራዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ በጽኑ አወገዘ

የአማራ ብሔረዊ ንቅናቄ–አብን የትግራይ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ የራያ አማራዎች ላይ እያደረሱ ያለውን ጭፍጨፋ በጽኑ ያወግዛል። የፌዴራል መንግስትና የአማራ ክልላዊ መንግስት የትግራይ ክልላዊ መንግስት እያደረገ ያለውን ዘር ተኮር የአማራዎች ግድያ ጣልቃ ገብተው እንዲያስቆሙና ጭፍጨፋውን የመሩና ትዕዛዝ የሰጡ የክልሉ መንግስት አመራሮችን ለሕግ እንዲያቀርቡ አብን ይጠይቃል።

መላው አማራ ከራያ አማራዎች ጎን እንዲቆም፥ የሰብአዊ መብት ተቋማትና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም የትግራይ ክልላዊ መንግስት አማራዎች ላይ እያደረገ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እንዲያወግዙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

አማራ በልጆቹ ትግል ታሪኩን ያድሳል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.