ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች የትግራይ ልዩ ኃይል በመከላኪያ ጥረት ከአካባቢው እየወጣ መሆኑ ከስፍራው በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል

በእርግጥ የተፈፀመው ግፍ በቪዲዮ ይሄን ይመስላል !ራያ አላማጣ ላይ የትግራይ ልዩ ሀይል ከተማዋን በጭስ አፍኗቷል ፣ልዩ ሀይሉ ወደ ህዝብ በመተኮስ ላይ ይገኛል ፣ የፌደራል መንግስት በራያ ህዝብ ላይ በወንበዴው የህውሓት መንግስት እየተደረገ ያለውን አፈና ሊያስቆም ይገቧል ገለልተኛ የሆነ የፀጥታ ሀይል በቦታው በማስፈር የክልሉን ልዩ ሀይል አኳባቢውን ለቆ እንዲወጣ ቢያደርግ ህዝቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን መከራ መቀነስ ይችሏል ። ባለው መረጃ አስራ አንድ ሰው በትግራይ ልዩ ሀይል ተገሎል ፍትህ ለራያ

Posted by Tilaye ZE on Sunday, October 21, 2018

ከሆስፒታል በደረሰን መረጃ #አምስት ወጣቶች በልዩ ሃይሉ ተገድለዋል

#ሁለት ወጣቶች በሞት አፋፍ ይገኛሉ (Critical)

= በጥይት የቆሰሉ በርካቶች ሲሆኑ ከተለያየ የከተማዋ አቅጣጫ ወደ ሆስፒታል እና ክሊኒኮች እየገቡ ይገኛል
– – – – – –
ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ “ለማንነት መከበር እስከ መስዋዕትነት” በሚል መፈክር በቆራጥነት እየታገለ ይገኛል!!! ከዚህ በሗላ ባርነት በቃን! መታሰር በቃን! መሞት በቃን! መረገጥ በቃን ብሏል!!! ማንነቴን ወይም ሞቴን ብሎ ቆርጦም ተነስቷል። ደግሞም በየትኛውም ጊዜ ህዝብ ያሸንፋል!!!!

መከላከያ ሰራዊቱ ሲገባም “መከላከያ የእኛ” እያለ ህዝቡ የተቀበለው ሲሆን በዚህ ሰዓት አንፃራዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ያለው ሰፈር ቢኖርም 01 ቀበሌና ወደ ላይ ያለው ሰፈር ግን አንዳች እንቅስቃሴ የሚባል የለም!!!
Dejene Assefa

አላማጣ በአሁኑ ሰዐት መከላኪያ ድንጋይ በመልቀም መንገድ በመክፈት ህዝቡን በማረጋጋት ላይ ይገኛል አንድ ወጣት ከጥቂት ደቂቃ በፊት በጥይት ተመቶ ወደ ሆስፒታል ገብታል የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው የራያ እናቶች በልጆቻቸው ሞት የመረረ ለቅሶ ላይ ናቸው ፡፡ ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች የትግራይ ልዩ ኃይል በመከላኪያ ጥረት ከአካባቢው እየወጣ መሆኑ ከስፍራው በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል በትህምክት ያበጠው ህወሓት ፋሽስታዊ ውንብድናው በራያ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ዝም አንልም!! ፍትህ ለራያ ህዝብ!
ስንታየሁ ቸኮል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.