ደውሉ ለማን ነው? For Whom The Bell Tolls? ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ክፍል አንድ ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

{1} ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ  (ህግሓት) ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ለመውጥት ሲታገል ቆይቶ በሜይ 24 ቀን 1993 እኤአ ነፃ ወጥታለች፡፡ (ህግሓት) አንድ አውራ መንግሥት ብቸኛ መንግሥት ሲሆን እስካሁን ምርጫና ሕገ መንግስት ገለመሌ የሚባል ዜና ፖለቲካ ሃተታ የለም፡፡ የህግሓት መንግስት የስብዓዊ መብት ምሃደር በዓለማችን ካሉት የመጨረሻ ደረጃ ትገኛለች፡፡ የኤርትራ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃንና ፕሬስ ነፃነት በዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ማህደር በመጨረሻነት ደቡብ ኮሪያን አስከትላ ገብታለች፡፡ የኤርትራ መንግስት የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ኢጋድ እንዲሁም በአረብ ሊግ በታዛቢነት አባል ነች፡፡ ኤርትራ 117,600 ኪሎሜትር ስኩየር የቆዳ ስፋት አላት፣ኤርትራ ህብረ ብሄር ሀገር ስትሆን የህዝብ የቌንቌ ስብጥር ዘጠኝ ዘውጌ ቡድኖች ይገኛሉ ከነዚህ ውስጥ፣ ትግርኛ 55 በመቶ፣ ትግረ 30 በመቶ፣ ሳሆ 4 በመቶ፣ ኩናማ 2 በመቶ፣ ቢለን 2 በመቶ፣ ራሻይዳ 2 በመቶ እንዲሁም የተለያዩ 5 በመቶ ዘውጌ ብሄር ብሄረሰቦች ቢኖሩም በዘር መደራጀትና እራስን በራስ እስከመገንጠል መብት የሚባል ገለመሌ የለም፡፡ በ2016 እኤአ የሥነ-ህዝብ ብዛት 4,954,645 ሚሊዮን ይገመታል፡፡  የኤርትራ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) በ2018 እኤአ  6 ቢሊዮን 856 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን የነፍስ ወከፍ ገቢ 988 ዶላር በአመት ይገመታል፡፡ The Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) was an armed organization that fought for the independence of Eritrean from Ethiopia.  ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ደሃ አገራት ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበሮች ባድማ፣ ፆረና፣ ኢሮፕ  ወስን ግጭት የተነሳ የኢትዮጵያ ህወሓት መለስ ዜናዊና የህጋሓት ኢሳያስ አፈወርቂ  ከ1998 እስከ 2000 እኤአ ጦርነት ገጠሙ፣  ከ70 እስከ 100 ሽህ ወታደሮቻቸውን በጦርነቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡   ጦርነት ‹‹ መቼም የትም አይደገም!!! ›› በሁለቱ አገሮች መታወሻ ቀን በጋራ እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡ ለኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን  ወንድማማቾች የጦርነቱ ሠማዕታት መታሰቢያ ሙዝየም ይቆቆም እንላለን፡፡በ2018 እኤአ በሁለቱ ሃገራት እርቀ ሰላም በዶክተር አብይ አህመድ አመራር ሠላም ሠፈነ፡፡

በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣ (Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የትግራይ ክልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የአፋር ከልል 6 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የጋምቤላ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሃረሪ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉዋቸው፡፡  በኢትጵያ የክልል ብሄራዊ መንግሥታት  የመስፋፋት ፖሊሰ፣ ሃገሪቱን ወደ ማያባራ የድንበርና የወሰን ግጭት እንደሚዳርጋት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡ ፌዴራሊዝም በጂኦግራፊያዊ ወይስ በቌንቌ!!!

{2} የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣የትግራይ ክልል አራት አዋሳኝ ወይም ድንበርተኞች አሉት እነዚህም   በሰሜን ከኤርትራ፣ በምሥራቅ ከአፋር ክልል፣ በደቡብ ከአማራ ክልል  እንዲሁም በምዕራብ ‹‹ከሱዳን ሪፐብሊክ›› ጋር ይዋሰናል፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ድንበር  የማስፋፋት ፖሊሰ  ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከአፋር ህዝብ ለም መሬት በመንጠቅ ወደ ትግራይ ክልል በማካተት የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ደሃ ወንድሞቹና እህቶቹ የማለያየት ፖሊሲ ውጤት ነው፡፡ ከጎንደር መሬት ሁመራ፣ ወልቃይት ወዘተ የሠሊጥ ለም መሬት ላይ የትግራይ የጦር ጉዳተኛችን በማስፈር፣ የአገሬውን መሬት በግፍ በመንጠቅ የተቃወመውን ህዝብ በመግደል፣ በማሰር እንዲሰደድ በማድረግ ኃብቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ ከአፋር የጨው ማዕድናት ፋብሪካዎች በመትከል አብዛኛዎቹን የሚቆጣጠሩት የትግራይ ጦር አበጋዞች ናቸው፡፡ እንዲሁም በአፋር የተገኘውን የፖታሽ ማዕድን አምርቶ ለመሸጥ በአፋር በኩል በትግራይ አርጎ ጅቡቲ የሚገባ የባቡር መስመር ዝርጋታ የህወሓት ጦር አበጋዞቹ የኃብት ቅርምትና የመስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂ ውጤት ነው፡፡ ህወሓት ከአጎራባች ድንበርተኞቹ ላይ የሚያደርገው የወንድማማች ጦርነት ጊዜ ቆጥሮ ለፀፀት ይዳርገዋል፣ ከኤርትራ ጦርነት ትምህርት ወስደን የትግራይ ክልል ከጎረቤት ክልሎች ጋር ያለው የወሰን ግጭት በሃገሪቱ ሽማግሌዎች እንዲፈታ በማድረግ ሠላም እንዲሰፍን ማድረግ ይቻላል፡፡ በጦርነት የሚማገዱት  የደሃው ህብረተሰብ ልጆች ሠላም አግኝተው የሃገራቸው ኢኮኖሚን ገንብተው እንዲኖሩ መመኘትና መድረግ ይቻላል፡፡ ሃገራችን ሃብታም ናት፣ ለሁላችንም ትበቃለች፣ ሁሉም ዜጋ በመላ ሃገሪቱ ተዘዋውሮ መስራትና ሃብት ማፍራት እስከቻለ ድረስ የክልሎች ድንበርና ወሰን አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሁሉም ክልሎች የባህር ማዶ ኢንቨሰተሮች ክልላቸው ገብተው  እንዲሰሩ እያማለሉ ስለምን ሃገር በቀል ኢንቨስተር በሃገሩ ባይታውርና ሁለተኛ ዜጋ ይሆናል፡፡

{3} የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር፣በ1973 አኤአ ተመሰረተ የአቢሲኒያን/ የኢትዮጵያን የቅኝ ገዥዎችን ሥርዓት ለመታገል የኦሮሞ ብሄርተኞች ትግል ጀመሩ ይላል የኦነግ በይነ መረብ ድረገፅ መረጃ፡፡  The Oromo Liberation Front (OLF) is a political organization established in 1973 by Oromo nationalists to led the national liberation struggle of the Oromo people against the Abyssinian colonial rule. የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ዘጠኝ አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፡፡ የኦሮሚያ ክልል በሰሜን  ከአፋር፣ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ክልሎች፣ በምስራቅ ከሶማሌ ክልል፣ በምዕራብ ከሱዳን ሪፓብሊክ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ክልል፣ እንዲሁም በደቡብ ከኬንያና ከጋምቤላ ክልል ጋር ይዋሰናል፡፡ በመስከረም 2011 ዓ/ም ኦሮሚያና  በቢኒሸንጉል ክልል ከ100 እስከ 150 ሽህ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡  የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር፣ በሠላም ገብቶ ለምን ትጥቅ አልፈታም ይላል?

{4} የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር፣ (ኦብነግ) የሶማሌ ክልል ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ‹‹ህዝበ ውሳኔ››(ሪፍረንደም) እንዲያደርግ ጠይቆል፡፡ ኦብነግ በዓለም አቀፍ ህግ የሚታወቀውንና በኢትዮጵያ ህገመንግሥት ላይ ያለውን  ‹‹ራስን በእራስ የማስተዳደር መብት›› እንዲከበር ለብሉንበርግ ዜና ገልፆል፡፡ According to a news report by Bloomberg published today the Ogaden National Liberation Front, ONLF will demand a referendum on self-determination for Somali region. “We want to achieve self-determination recognized by international law under the current Ethiopian constitution. … We want our people to have a right to decide. ’’Ahmed Yassin Abdi, the ONLF’s foreign secretary. Tigrai Online, (Sept.18, 2018) የሱማሌ ከልል አምስት አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የሱማሌ ክልል በምዕራብ ከኦሮሚያ ክልል፣በሰሜን ከአፋር ክልል እና ከጅቡቲ ሪፓብሊክ ፣ በደቡብ ኬንያ እና በደቡብ እና በደቡብ ምሥራቅ ከሶማሊያ ጋር ይዋሰናል፡፡ የሱህዴፓ የሱማሌ ክልል መንግሥት፣ በምሥራቅ የሃገራችን ክፍል ይገኛል፡፡ በሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የድንበር ግጭት ዜጎቻችን ሞተዋል፣ ብዙ ንብረት ወድሞል፡፡ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ህዝብ በሁለቱም ወገኞች ተፈናቅለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በጂኦግራፊያዊ አከላለል ላይ እንደቀድሞው ቢከፋፈል ግጭት ይጠፋል፡፡ ክልሎችን በዘር እና በቌንቌ በድንበር መለየት የግጭቱ መነሻ ነው፡፡ ደውሉ ለማን ነው? For whom the bell tolls? የጦርነቱ ደውል ለማን ነው? የቀብሩ ደውል ወንድምህን ለመቅበር ነው?

እስራት፣ ግርፋት፣ የዘር ፍጅት፣ የጥላቻ ንግግር፣ ጦርነት፣ ስደት ‹‹መቼም የትም አይደገም!!! Never Ever Again!!!››

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.