“ይቅርታ ባለመጠየቃቸው በጣም ደስ ብሎኛል”- የአቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናት

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውንና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። የአቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናት ወ/ሮ ብዕዓት ኃይለጊዮርጊስ፤ “እኛም ቤተሰቦቹ ሆነ እርሱ ብዙ መሰዋትነት ከፍለናል። ስለዚህ ይቅርታ ባለመጠየቃቸው በጣም ደስ ብሎኛል።” ብለዋል።

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የይቅርታና የክስ ማቋረጥ እንደሚያደርግ በወሰነው መሰረት እስረኞች ከእስር መለቀቅ መጀመራቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እያስታወቀ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቹ የግንቦት ሰባት አባል መሆቻቸውን አምነው እንዲፈርሙ ሲጠየቁ፣ የተወሰኑት እስረኞች ክሳቸው ሲቋረጥ ሌሎቹ ደግሞ የይቅርታ ደብዳቤ እየፈረሙ እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ይናገራሉ። አንዳንዶቹ ከማረሚያ ቤት ወጥተው ለተሃድሶ ስልጠና መግባታቸውም እየተሰማ ነው።ጽዮን ግርማ የተወሰኑትን የእስረኛ ቤተሰቦች አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች። – ጽዮን ግርማ (VOA Amharic)

[jwplayer mediaid=”50392″]

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.