ሰበር ዜና – በዝቋላ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ

ሐራ ዘተዋሕዶ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡

ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡

የቃጠሎው መንሥኤ በውል ባይታወቅም ቃጠሎው በአካባቢው ባለው ከባድ የነፋስ ኃይል ሳይፋፋ እንዳልቀረ ተሰግቷል፡፡

የአቅራቢያው ነዋሪ ኅብረተሰብ በጥሩንባ በተላለፈው የድረሱልን ጥሪ የተሰባሰበ ሲኾን ወደ ወረዳው አስተዳደርም ተደውሎ የፖሊስ ኃይል በስፍራው መድረሱ ተገልጧል፡፡

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.