ወያኔያን የማንን ሀገር ነው እንገነጥላለን የሚሉት??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው )

ሰሞኑን እነ ወያኔ ለመልካም ነገር ሲጥሩ እንደቆዩ ሁሉ “…የማይሆን ከሆነ ምን አደከመን አንገነጠልም እንዴ!” ብለው ምድረ ትግሬን “ምን ይውጠናል? ምን እንበላለን፣ ምንጠጣለን? እንዴት እንኖራለን?…!” አሰኝተው አስደንግጠውታል፡፡

በርካታ ሰዎች እነ ወያኔ ይሄንን ነገር ለቀልድ ያህል ወይም የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማስደንገጥ ያህል ብቻ የተናገሩት መስሏቸዋል፡፡ እውነቱ ግን ቀልድም አይደለም ለማስደንገጥም አይደለም፡፡ ይህ የመገንጠል አማራጭ ወያኔ ከተጠያቂነት ማምለጫ አድርጎ የሚያስበው ብቸኛው መንገዱ ነው፡፡ በመሆኑም ዕድሜው የሚያጥርበት አጋጣሚ ቢፈጠር ከተጠያቂነት ለማምለጥ ፈጥኖ የሚወስደው እርምጃ ቢኖር ትግራይን መገንጠል ነው፡፡ ሲገነጠልም ከተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል አይደለም የሚገነጠለው፡፡ እንደዚህ የሚመስላቸው በርካታ የዋሀን ወገኖች አሉ፡፡ ከዚህ የተሳሳተ አስተሳሰባቸውም ተነሥተው “ውይ ምነው እንዲያው በተገነጠሉና በገላገለን!” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ እንደዚያ አይደለም ወያኔ የሚያደርገው፡፡ ወያኔ ለመገንጠል የሚያስበው ኢትዮጵያን አፈራርሶ ነው፡፡ ቀሪዋን ኢትዮጵያን እንዳለች ትቶ ቢገነጠል ምን እንደሚከተለው ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡

አንዱ ወያኔ ይሄን የመገንጠል ነገር ነጻ ጋዜጠኛ ነኝ ለሚል የወያኔ ሰላይ የማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ ሹክ ማለቱን ተከትሎ በርካቶች “እንዴ! እንዴት? ትግራይ እኮ የኢትዮጵያ መሠረት ነች! ፣ የኢትዮጵያ መሠረት ከሆነ ሕዝብ እንዴት እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ይወጣል? የአክሱም ሥርዎ መንግሥት፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አክሱም ጽዮን….!” ምንትስ ምንትስ እያሉ ለማግባባት ሲጥሩ ተስተውለዋል፡፡

ይሄ ነገር ማለቴ ትግሬን የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ባለቤት አድርጎ የመሣሉ ነገር ባለማወቅ በሚፈጸም ስሕተትና በማወቅ በሚፈጸም ስሕተት በሁለቱ ምክንያቶች የሚነገር ቃል ነው፡፡ 1ኛ. ትግሮች አሁን ላይ በአካባቢው መገኘታቸው ጠልቀው መመርመር በማይችሉ ወገኖች በፈጠረው የተሳሳተ ግምት 2ኛ. ከጥንት ጀምሮ ባዕዳን ሀገራችንን ለመውረር በመጡ ቁጥር ከዐፄ ሠርፀድንግል ዘመን ጀምሮ ትግሮች በባንዳነት ለባዕዳን እየተሰለፉ ሀገራችንን፣ ሕዝቧንና መንግሥቷን በተደጋጋሚ እየወጉ ስለሚያስቸግሩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ ከዚህ የጥፋት ተግባራቸው እንዲታቀቡ ለማድረግ ታስቦ ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል ነው፡፡

በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች አክሱም የትግሬ እንደሆነ ተደርጎ የሚነገረው ነገር እያደር እውነት እየመሰለ መጥቶ ዛሬ ላይ ሁሉም እንደ እውነት የሚያወራው ነገር ሆኖ ቁጭ ብሏል፡፡ ነገር ግን ትግሮች የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ አንድም እንኳ ቁሳዊም ሆነ ትውፊታዊ ማስረጃ ተገኝቶ አያውቅም፡፡ ማስረጃዎችና ትውፊት የሚያረጋግጡት አክሱም የአማራ መሆኑን ነው፡፡

የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት ደብዳቤ ይጻጻፉ የነበረው፣ የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት “በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው?” ብለው ጠይቀዋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ አማርኛ የአክሱማውያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለጠያቂዎቹ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ “አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ!” ወይም “አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው!” የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሔዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ትግሬ ጸሐፊም ትውፊትንና ዋቢ መጻሕፍትን በመጥቀስ “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ይሄንን ገልጸውታል፡፡

የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የምሥጢር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ እንደነበረ ይነገራል፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ናቸው፡፡ ግእዝ ካልሆኑም አማርኛ ናቸው፡፡ አንድም የትግርኛ ሥያሜ ያለው ንጉሥ የለም፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቃላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡

ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ፦ ምኒልክ (ምን ይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬ ንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬ ንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማ አስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰን ሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማ አስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳ ውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድል ነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ቀድሞ ነገር የአክሱማውያንን ሥርዎ መንግሥት የሚጨምረው የንጉሥ ሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያው፣ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ደግሞ የመጨረሻው የሆኑበት ሰሎሞናዊውን ሥርዎ መንግሥት በመሀል ሌላ ዘር እንዲወስደው ወይም እንዲጠልፈውና የዚሁ ሥርዎ መንግሥት አካል ተደርጎ እንዲቆጠር የሚፈቅድ ወይም ዕድል የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት የነበሩት ነገሥታትና ንግሥታት ሥልጣን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍበት ሥርዓት ስለነበረ የነበረው ሁሉም የአንድ ዘር ተወላጆች ከአንድ ዘርም የአንድ ቤተሰብ ተወላጆች ብቻ እንዲሆኑ ያደረገ ስለነበረ ነው፡፡ ምንም እንኳ አንዳንዴ ከሌላ ዘር በጋብቻ ምክንያት የመቀላቀል አጋጣሚ የነበረ ቢሆንም ቅሉ፡፡

ከዚህም ሌላ ከ912ዓ.ም.-1245ዓ.ም. ድረስ ለ333 ዓመታት ያህል አገዎቹ ሥልጣን ወስደው ነበረ፡፡ ይሁን እንጅ መንግሥታቸው የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት ተባለ እንጅ ሰሎሞናዊ አልተባለም፡፡ መጨረሻም ላይ “መንግሥትን ለሰሎሞናዊው መልሱ!” ተብለው እንዲመልሱ ተደርገዋል፡፡ በመሆኑም ትግሬ የሰሎሞናዊውን ሥርዎ መንግሥት ሊይዝ የሚችልበት ዕድል አልነበረም፡፡ ለዛም ነው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ለመንገሥ ዝግጅት ያደርጉ በነበሩበት ጊዜ የዘር ኃረጋቸውን ከዐፄ ፋሲል ጋር አያይዘው በመቁጠር ንግሥናው እንደሚገባቸው ጥረት ያደርጉ የነበረው፡፡

እንዲህ ከሆነ ታዲያ ትግሮች እነማን ናቸው? ትግሬ ማለትስ ምን ማለት ነው? ከየት በማን ዘመን መጡ? ማስረጃዎችስ ምን ምን ናቸው? አማራ እንዴት መቸና በምን ምክንያት ከአክሱም ሊጠፋ ቻለ? የመሳሰሉ ጥያቄዎችን የሚመልሱላቹህን ከዓመታት በፊትና አንድ ሌላ ደግሞ ታች አምና የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ሊንኮች (ይዞች) አያይዠላቹሀለሁና ተጭናቹህ በማንበብ እውነቱን ለመረዳት እንድትችሉ እጋብዛለሁ፡፡

እንዲያው ግን ቆይ እናንተ ስታስቡት ትግሮች የዚያ ገናና የአክሱም ታሪክ ባለቤት ቢሆኑ ነው ወይ ለዚህች ሀገርና ለታሪኳ ከጥንት ጀምሮ ጠንቅ ነቀርሳ ጠላት የሚሆኑት??? ያንን ያህል የለፉ፣ የደከሙ፣ የወጡ የወረዱ፣ መሥዋዕትነት የከፈሉ ቢሆኑማ ኖሮ ልክ አማራ እንደሚያደርገው ለዚህች ሀገር የባለአደራነት ስሜት ይሰማቸው፣ ተቆርቋሪ፣ አሳቢ ይሆኑ ነበረ እንጅ እንደምናያቸው ቅንጣት ታክል የማይሰማቸው ዴንታቢሶች፣ ለሀገር የሚቆረቆረውን የሚያስበውን እየመነጠሩ አጥፊዎች መንጣሪዎች ይሆኑ ነበረ??? ልክ እንደ አማራ የሀገሪቱ አንድነትና የህልውናዋ ነገር የሚያሳስባቸው፣ እረፍት የሚነሳቸው፣ የሚያስጨንቃቸው ይሆኑ ነበር እንጅ ሀገሪቱን ለማፈራረስና ለማጥፋት ሌት ተቀን ሳይሰለቹ የሚማስኑ ጠንቆች ይሆኑ ነበረ??? ፣ ልክ በአማራ ላይ እንደሚታየው ከጎጥ በላይ ኢትዮጵያን ከዘር በላይ ኢትዮጵያዊነትን የሚያስቀድሙ ይሆኑ ነበረ እንጅ ጠባብ ጎጠኛና ዘረኛ ይሆኑ ነበረ???፣ እንደ አማራ የሀገራችንንና የሕዝቧን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ለማስከበር የሚዋደቁ፣ የሚታትሩ፣ የሚማስኑ ይሆኑ ነበረ እንጅ ለጠባብ ጎጠኛ ጥቅማቸው ሲሉ በ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” አስተሳሰባቸው የሀገርንና የሕዝቧን ብሔራዊ ጥቅሞች ቅንጣትም ሳይሰማቸው ለባዕዳን አሳልፈው የሚሰጡ ይሆኑ ነበረ??? ትግሮች የምናውቃቸውንና የምናያቸውን ሊሆኑ የቻሉት ለዚህች ሀገር የደከሙ፣ የወጡ የወረዱ፣ መሥዋዕትነትን የከፈሉ ስላልሆኑ ይሄ የሥነልቡና ውርስ ስለሌላቸውና በባሪያነታቸው ሀገሪቱን የጠላት ሀገር አድርገው ስለሚያዩዋት ነው፡፡ እውነቱ ይሄው ነው፡፡ የሥነ ልቡና ውርስና የታሪክ እርሾ ቢኖራቸው ኖሮ በምንም ተአምር እንዲህ ሊሆኑ ባልቻሉ ነበረ፡፡

በመሆኑም ትግሮች ሆይ! ሀገራችን ካልተመቸቻቹህ ሀገራችንን ለቃቹህ ወደመጣቹህበት ውልቅ ትላላቹህ እንጅ “እንገነጥላለን!” ምንትስ እያላቹህ ልትደነፉብን የምትችሉበት ምንም ዓይነት የሞራል (የቅስም) ብቃት ጨርሶ የላቹህምና እረፉ! አደብ ገዝታቹህ ትቀመጡ እንደሆነ ተቀመጡ! ካልሆነ ግን ዋ! ኋላ!!!

ሊንኮቹ (ይዞቹ) የሚከተሉት ናቸው፦

http://www.satenaw.com/amharic/የዘር-ማጥፋት-ወንጀሎች-በአማራ-ሕዝብ-ላይ/

ሁለተኛው ደግሞ፦

http://www.satenaw.com/amharic/የአማራ-ሕዝብ-ማንነትና-አስቂኙ-የዘመኑ-የ/

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.