ሰፌ ደጎቻ ቀበሌ ሌሊቱን 5 ቤት ተቃጥሎ አድሯል፤

በአብዛኛው የጮራና የዲጋ ወረዳዎች ሌሊቱን የተረጋጋ ቢሆን በሰፊ ደጎቻ ቀበሌ የ5 ዐማሮች ቤት ተቃጥሎ አድሯል። ነዋሪዎች በአካባቢው ፀጥታ ሊያስከብር የሚችል አካል እንዲገባ ጠይቀዋል።

በሌሎቹ አካባቢዎች ነገሮች ሌሊቱን ተረጋግተው ማደራቸው ተስፋ ሰጪ ሲሆን የአካባቢው ሽማግሌዎች በማረጋጋት በኩል ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

Muluken Tesfaw

 

የጮራ ወረዳ አስተዳዳሪ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስን መልሷል፤ ግጭቱ ባልተነሳባቸው አካባቢዎችም ዐማሮች በቀበሌ ቤቶች ታጉረዋል፡፡
 ጉዳዩን ለማጣራት የሄዱ የዐማራ ወጣቶች ጂማ ከተማ ላይ ተመልሰዋል

በኤሊባቦር ዲጋና ጮራ ወረዳዎች በዐማሮች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ዛሬም አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ወደ ጮራ የገጠር አካባቢዎች ቢሔድም የወረዳው አስተዳዳሪ ገጠር ችግር የለም፤ በከተማው አካባቢ የተወሰነ ነበር አሁን ተረጋግቷል በሚል መልሷቸዋል፡፡ ሆኖም በጮራና በዲጋ ወረዳዎች ችግሩ መባባሱንና የሞቱ ሰዎችም ቁጥር ብዙ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ 
ዛሬ ዲማ ጋዮ በተባለ አካባቢ በዐማሮች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በርትቶ መዋሉን የሚገልጹት ተጎጂዎች በጫካ ውስጥ ከተደበቁት መካከል ‹‹ልጄ ምነው ዐማራ የሚቆረቆር ልጅ አላፈራም? ይህን ከማይ እድሜ ባይረዝም ምን አለበት?…›› ሲሉ በሲቃ በስልክ ያነጋገርናቸው እናት እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ ገልጸዋል፡፡
በሁለቱም ወረዳዎች ከ15 ሺህ በላይ ዐማሮች መፈናቀላቸውን የሚገልጹት ምስክሮች በምግብ እጦት የታመሙ ሕጻናት ሁሉ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ችግር ሊከሰት ይችላል በሚል የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የዐማራ ተወላጆችን ከቤታቸው ወጥተው በቀበሌ ጸ/ቤቶችና በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡ ሆኖም በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚገልጹት በቀበሌዎች የተዘጉ ሰዎች ሕይወታቸው የበለጠ ስጋት ላይ መሆኑን ይናገራሉ- ‹‹በቂ ገለልተኛ ጥበቃ ስለሌለ በአንድ እንደተዘጉ በጅምላ የማለቅ እድል አላቸው›› በማለት፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ወደ ኤሊባቦር ጉዳዩን በቅርበት ለማጣራት የሄዱት የዐማራ ወጣቶች ጂማ ላይ ተመልሰዋል፡፡ ጂማ ከተማ ደርሰው ለመመለሳቸው እንደምክንያት ያቀረቡት ጠጉረ ልውጥ ሆናችሁ ብትገኙ ችግሩን የፈጠሩት እነሱ ናቸው በሚል የኦሕዴድ ባለስልጣናት ያስሯችኋል ተብለን ነው ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ የኦሕዴድ አመራሮች ቀስቃሽነት በዐማሮች ላይ ጥቃት ሲደርስ በሦስት ወር ውስጥ ይህ ሦስተኛው ነው፡፡ በነሐሴ ወር በጂማ ዞን ጦላይ ወረዳ የበርካታ ዐማሮች ቤትና ንብረት ወድሞ የሰው ሕይወትም መጥፋቱ የሚታወስ ሲሆን ከመስከረም ጀምሮ ደግሞ በሊሙ ከሣ የተጀመረው ጥቃት እስካሁን አልቆመም፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ምስሎች በጦላይ በነሐሴ ወር የወደመ የዐማሮች ቤትና ንብረት ነው፡፡

 

Muluken TesfawNo automatic alt text available.
Image may contain: tree, sky, plant, outdoor and nature
Image may contain: plant and outdoor
Image may contain: outdoor

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.