አማራን በአማርኛ ተናጋሪ የህወሃት ክንፍ በብአዴን ስም እየገዛ ያለው የትግሬ ወያኔ በአማራ ህዝብ ተስፋ እየቆረጠ ነው። (ቤሮኒካ መላኩ)

ትግሬ ወያኔ በአማራ ህዝብ ተስፋ ከቆረጠ ቆዬ ። አማራ የፈለገውን ፕሮፓጋንዳና ማባበያ ቢጠቀም እንደማይለቀው በደንብ ተገንዝቧል ። በዚህም መሰረት ያለው አማራጭ ለአማራ ህዝብ ጠላት መሸመት ነው። እስካሁን ድረስ ለ25 አመታት ለአማራ ህዝብ ጠላት የሚሆን ሲሸምትለት ኖሯል ። ለመጀመሪያ ጊዜ በርካሽ ዋጋ የተገዛው ጠላት ኦነግ የሚባል የዘገምተኞች ስብስብ ነበር ። ይሄ በትግሬ የተገዛው ኦነግ ከ24 አመታት በፊት አርባጉጉና በደኖ በህፃናት ፣ በአረጋውያንና በሴቶች ላይ ግፍ ፈፅሞ የአማራ ጠላትነቱን አረጋገጠ ። ከዛም በኋላ ትግሬ በእጅ አዙር እና በቀጥታ አማራን ሳያስገድል ውሎ አያድርም።

አሁን ትግሬ ወያኔ የመጨረሻውን ካርድ እየመዘዘ ይመስላል። ጉራጌ እና አማራ የሚል ። መቼም አስቤው የማላውቀው ነገር።

ወያኔ ከአማራ ቀጥሎ የሚጠላው እና እንደ ጠላት የተመዘገበ ዘር ቢኖር ጉራጌ ነው። ወያኔ ለጉራጌዎች የሰጠው ስም እንኳን ” ተለጣፊ ነፍጠኛ ” የሚል ነበር። ይሄን የሚልበት ምክንያት ከአማራ ጋር ያላቸውን እጅግ የጠበቀ ግንኙነት ለመጠቆም የሚጠቀምበት ነው።
ወያኔ ገና ከበርሃ ሲመጣ ራሱ መፈክሩ እና አላማው ” ፖለቲካውን ከአማራ ንግዱን እና ሃብቱን ከጉራጌ ነጥቆ መቆጣጠር ” የሚል እንደሆነና ተግባራዊ እንዳደረገው ግልፅ ነው።

ባለፉት አመታት አዋሳኝ ከሆኑት ከኦሮምያ ክልል አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የተለያዩ ግፎች እና እንግልት ሲደርስባቸው ፣በተለያየ ወቅት በተፈጠረዉ መከራ አማራዉ ቤቱ በላዩ ሲቃጠል የደረሰለት ጉራጌ ነበር። ለዘመናት በአማራ እና በጉራጌ መካከል ያለው ትስስር በቃላት መግለፅ ይከብዳል ።

ዛሬ ወልቂጤ ውስጥ አማራ “በጉራጌ ” እንደተገደለ ሰማን ። ቤታቸው “በጉራጌ ” የተቃጠለና የተዘረፈ አማሮች ብዙ እንደሆኑ ሰማሁ ። እቅዱ እና አስፈፃሚው ማን እንደሆነ እናውቃለን ። ይሄን የትግሬ እቅድ ወደ ተግባር የሚቀይር ሆዳም ወይም ኢያጎ የሆነ ጉራጌ አይጠፋም ። ይሄ ተግባር ግን የጉራጌን ህዝብ የሚወክል ፈፅሞ አይደለም ።

ጉራጌ ከአማራው በበለጠ በተለያየ የኢትዮጵያ ክልሎች ከትግራይ ክልል በቀር በሥራ ሃገሬ ነው ብሎ የሚኖር ህዝብ ነው ። ይሄ ህዝብ በቤቱ በዞኑ እንደዚህ ግፍ የሚሰራበት አመክንዮ አንድም አይኖርም ።

ጉራጌ በሱማሌ ክልል፣ በድሬዳዋ እና በሐረር በደብረዘይት ፣ በጂማ እና ፣ በወለጋ በሙሉ ንብረታቸው ተውስዶ ባዶ ቀርተዋል። “ተለጣፊ ነፍጠኛ ” እየተባሉ በወያኔ የሚጠሩት እና “የነፍጠኛ አማራ ” አጋር ተብለው በአቢዮታዊ ዴሞክረሲ መዝገብ ውስጥ የሰፈሩት ጉራጌዎችን ከአማራ ህዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር ለመበጠስ የተደረገች ሴራ ነች።
በመሰረቱ ይች ሴራ የተጀመረችው 1997 ቅንጅት አገር ማንቀጥቀጡን ተከትሎ ነበር። በወያኔ አመለካከት “ቅንጅት” አማራና ጉራጌ ትግሬን ለማጥፋት የተቀናጁ ናቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። አሁን ወያኔ ኦሮሞን በሱማሌ እንዳደረገው ሁሉ አማራን በጉራጌ እየሞከረ ነው ። የሚሳካ አይመስለኝም ።

በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው አለም አንድ ለዘመናት የሚነገር የፖለቲካ Maxim አለ… “ቋሚ ወዳጅና ቋሚ ጠላት የለም” የለም የሚል ። ይሄ የተለመደ አባባል በአማራና በሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ሊሰራ ይችላል ነገር ግን ይሄ አባባል በአማራና በትግሬ ወያኔ መካከል አይሰራም ። ትግሬ ወያኔ ለአማራ ቋሚ ጠላቱ ነው ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.