ሰበር መረጃ…..በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የህወሃት ቡድን ተቃዋሚዎች ከደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ ጄኔራል ጋር ዉይይት አደረጉ

የህወሃት ዘረኛ አገዛዝ በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመዉን የሰባዊ መብት ረገጣና ሐገር እና ህዝብን የማጥፋት ወንጀል ሲቃወሙ የነበሩና በመቃወም ላይ የሚገኙ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖችን ለማጥቃት አመመኝ ደከመኝ የማይለዉ የወያኔ የደህንነት ክንፍ ያሳለፍነዉ ሳምንት በ06/06/2016 እንዲሁም በ10/06/2016 ፕርቶሪያ የሚገኘዉ የህወሃት መጠቀሚያ ኢንባሲ ዉስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ 12 ግለሰቦችን ስም ዝርዝርና ፎቶ ግራፍ የያዘ ሰነድ ዳዊት በተባለ ተላላኪ ለደህንነቶች መቅረቡን ተንተርሶ  እጅግ የተቆጡ የደቡብ አፍሪካ ጀግኖች በትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን ላይ የሰበሰቡትን የቀደሙ እና  ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን በደቡብ አፍሪካ ለሚመለከተዉ ክፍል አቅርበዉ ዛሬ በ12/06/2016 ከፍተኛ ከሆኑ በፖሊስ ኮሚሽነር የበላይ አገልግሎት ተወካይ ከሆኑ  የፖሊስ ጄኔራሎች ጋር ተወያይተዋል።

በስብሰባዉ ላይ የቀረቡትን የተለያዩ ጥልቅ መረጃዎች ለደህንነት ሲባል ማዉጣቱ አስፈላጊ ባይሆንም በስብሰባዉ ላይ ከተነሱት ነጥቦች መካከል ” የሀወሃት መንግስት ዲሞክራሲያዊ መብታችንን ከመግፈፍ ባለፈ ሁኔታ በህይወታችን ላይ ሊያደርስ የሚችለዉን አደጋ ሸሽተን በተጠለልንበት ደቡብ አፍሪካ ድረስ ተከትሎን በመምጣት የሚፈጽማቸዉን የሞራል ጉዳት፣ የመኖር ህልዉና ጥቃት፣ የዛቻና የማስፈራራት ተግባራቶችን ባጋለጠ መልኩ ለሁለት ሰአታት ገለጻ የተደረገ ሲሆን በመንግስት ደረጃ የሚካሄዱ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝዉውርና አግባብ ያልሆኑ የገንዘብ አሰባሰብ መንገዶችን በተመለከተ ለሚመለተዉ አካል በምስልና በፎት የተደፉ መረጃዎች እንዲሁም የድምጽና የጽሁፍ ሰነዶች ተያይዘዉ ቀርበዋል።

በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ ጄኔራል አመራር የሆኑት ባለስልጣን እንዲህ ያሉ ክስተቶች በተለያዩ ሐገር ዜጎች ላይ የሚደርስ ቢሆንም የኢትዮጵያ ገዢ ስርአት ግን እየሄደበት ያለዉ መንገድ እጅግ አሳዛኝና የማያዋጣ ነዉ። በማለት ያስቀመጡ ሲሆን በዲፕሎማቲክ የደህንነትና የፖሊስ መረጃ ዉስጥ የሚሰሩ አንድ ኮረነ አክለዉ “በአስገራሚ ሁኔታ የራሱን ዜጎች በሆነዉ ባልሆነዉ በመክሰስ የዲፕሎማቲክ ክትትል ፖሊሶችን ጭምር ያማረረ መንግስት ነዉ ያላችሁ የሁለቱን ሐገሮች የህዝብ ደህንነትና አጠባበቅ ወይም ሐላፊነት የመዉስድ ግዴታዎችን የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት እንደተመለከተዉ ሊገባን አልቻለም ይህን የዘቀጠ መንግስታዊ ስህተት በዚህ ክ/ዘመን መመልክት የሚያሳዝን ነዉ። በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ስብሰባዉን በበላይነት ሲመራ የነበረዉ የፖሊስ አካል በቅርቡ ሊወሰድ የሚገባዉን እምጃና ጥንቃቄ እንደሚያሳዉቁ ጠቅሰዉ ስብሰባዉ በደቡብ አፍሪካ በኩል በዉስጥ እንደሚያዝ አስገንዝበዋል።

ድል ለኢኦጵያ ህዝብ ! !

ልዑል አለሜ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.