ኢትዮጲያዊያን ለለውጥ ቀን ተዘጋጁ (ከነፃነት ለኢትዮጲያ የቀረበ ጥሪ)

ሐምሌ 27፣ 2008 ዓ.ም

Ethioopia Freedom - satenawአገር በማስገንጠል የጀመረው ዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሃት-ወያኔ) በእናት አገራችን ኢትዮጲያና ህዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍና ሰቆቃ ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ኢትዮጲያዊ ሊታገሰው ከማይችለው ደረጃ ደርሷል። በተለያዩ የኦሮሞ አካባቢ፣ ህዝባችን የአጋዚ አነጣጣሪ ተኳሾች እየተጨፈጨፉ ነው። በወያኔ ጥይት የተበሳሳ፣በደም የተዘፈቀ የኢትዮጲያዊ ህጻናትና ወጣቶች አስከሬን ማየት የተለመደ ሆኗል። በአዲስ አበባ፣ በጋምቤላ በኦጋዴን፣ በሲዳሞ፣ በጎንደርና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች ወያኔወች የመብት ጥያቄ ያቀረቡ ብዙ ዜጎችን ተራ በተራ በግፍ ገድለዋል።  በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ወገኖቻችንን በእስርና በድብደባ እያሰቃዩ ነው። ብዙ ሺህወች የወያኔን ግፋዊ አገዛዝና ረገጣ በመሸሽ ከአገር ተሰደዋል፣ በአሰቃቂ ሁኔታም ተገድለዋል። ግፍ መሸከም ያልቻሉ ኢትዮጲያዊያን ራሳቸውን አቃጥለዋል። የአገሪቱን ስልጣን፣ ሃብት፣ ንግድና መሬት በወያኔ ድርጅቶችና በተወሰኑ የወያኔ የጥቅም ተካፋዮች ተቆጣጥረውታል።  ከሁሉም በላይ ወያኔወች በሚዘሩት መርዛማና ከፋፋይ የዘርና የጎሳ ፖለቲካ፣ የአገራችን ኢትዮጲያ አንድነት ከአደጋ ላይ ወድቋል።

በሌላ በኩል ይህ ከመጠን ያለፈና የሁሉንም ሰላማዊ ኢትዮጲያዊና የኢትዮጲያ አካባቢ ያዳረስ ግፍ ኢትዮጲያዊያንን ከምንጊዜውም በላይ ባንድ ሁነውና ተደራጅተው የወያኔን የግፍ አገዛዝ እንዲያወርዱ ነባራዊ ሁኔታን ፈጥሯል። ኢትዮጲያዊያን የደረሰባቸው መከራ ከምንጊዜውም በላይ አስተባብሯቸዋል። ማንኛውም ኢትዮጲያዊ የዚህ ታሪካዊ የህዝብ እንቅስቃሴ ተሳታፊ የመሆንና፣ አገርን ከጥፋት የማዳን ዜጋዊና ሰብአዊ ግዴታ አለበት።  ሌላው ታግሎ ነጻ ያወጣኛል በሚል ከዳር መቆም አገራችንን ወደ ከፋ አደጋ መውሰድ ይሆናል። ትዕግስት ከመጠን በላይ ሲያልፍ ፍርሃት እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም።

ስለዚህ ይህን ፋሽስታዊ የወያኔ አገዛ ከስልጣን ለማውረድና ሁሉም ኢትዮጲያዊ በነጻነትና በእኩልነት የሚኖርባት፣ አንድነቷና ሉአላዊነቷ የተጠበቀ፣ የህግ የበላይነት የሰፈነባት አገር እንዲትኖረን ለእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ የሚከተለው የትግል ጥሪ ቀርቧል።

  1. ሁሉም ኢትዮጲያዊ በዘር በጎሳ በሃይማኖት በአካባቢ ሳይከፋፈል በአንድ ጊዜ ለሚጠራ ለተቀነባበረ አገር አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቶ ይጠብቅ። ለዚህም ትግሉን በሰላማዊ መንገድ በየአካባቢው ለሚያስተባብሩ ጀግኖችና የቁርጥ ቀን ልጆች ድጋፋችሁን በተለያየ መንገድ እንዲትሰጡ። እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ የሌላውን ኢትዮጲያዊ ደህንነትና ህይወት ከወያኔ ሰርጎ ገቦችና ገዳዮች ይጠብቅ።
  2. አውቃችሁም ይሁን በአለማወቅ ከወያኔወች ጋር በማበር፣ የወገናችሁን ስቃይ በማብዛት ላይ ያላችሁ ሁሉ፣ ሚናችሁን የምትለዩበት ወሳኝ ወቅት አሁን ነው። በሰላም ለፍትህ ከሚታገለው ኢትዮጲያዊ ጎን ቁሙ።
  3. በጦሩ፣ ፖሊስና የወያኔ የስለላ መዋቅር ውስጥ ላላችሁ ሁሉ፣ ለሚያልፍ የወያኔ አገዛዝ ብላችሁና በጊዚያዊ ጥቅም ተገዝታችሁ የንጹሃን ወገኖቻችሁን ደም አታፍስሱ። ጊዜው የመርጃና የቴክኖሎጂ ዘመን በመሆኑ ዛሬ ያላችሁ ስልጣንና ጠብመንጃ ከነገ በህግ ተጠያቂነት አያድናችሁም።
  4. ለሃይማኖት መሪወች፣ የአገር ሽማግሌወችና ምሁራን፣ ይህ ለፍትህ፣ ለእውነት፣ ለዲሞክራሲና አገርን ለማዳን የሚደረግ ሰላማዊ ትግል መሆኑን አውቃችሁና፤ ለተገፋ ህዝብ መቆም የጽድቅ ስራ መሆኑን ተገንዝባችሁ፤ ያአቡነ ጴጥሮስን አርዓያ በመከተል በተቻላችሁ ሁሉ ህዝቡን ለነጻነቱ፣ ለእውነት፣ ለመብቱና ለአገሩ በአንድነት እንዲነሳ እንዲታስተባብሩ፣ ትግሉንም እንድትመሩ።
  5. የትግራይ ተውላጆች ሆይ፣ ወያኔወች በናንተ ስም ተነስተው፣ አገር ከመገንጠል አንስቶ፣ ህጻናትን በጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ እስከመግደል ብዙ ግፍ በኢትዮጲያ ላይ ፈጽመዋል። የብዙ ሺህወችን ህይወት መስዋእት አድርገውና የአገር ድንበር ለማስከበር የተሰለፈውን ኢትዮጵያዊ ጨፍጭፈው፣ ያአገሪቱን ስልጣንና ሃብት በመቆጣጠር፣ ዛሬ በሰላማዊ መንገድ መብቱን የሚጠይቀዉን ህዝብ በግፍ እየገደሉ ነው። ይህ የኢትዮጲያዊያን ስቃይ የናንተም መከራ መሆኑን ተገንዝባችሁ፣ የነዚህን አገር አፍራሾች ፈለግ ሳይሆን የጀግናው ራስ አሉላንና፣ ራሳቸውን ለኢትዮጲያ ዳር ድንበር የሰውቱን አጼ ዮሃንስ አርማ በመከተል አገራችንን ከጥፋት ለማድን በሚደረገው ትግል ተሰታፊ እንድትሆኑ።
  6. ወያኔወችና ከወያኔ ጋር በስልጣንና በጥቅም የተሳሰሩ ግለሰቦች ሃብታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከአገር ለማሸሽ በዝግጅት ላይ ናቸው። ይህን በመረዳት ማንኛውም ኢትዮጲያዊ የነዚህን ወንጀለኞችና የአገር ሃብት ዘራፊወች ንብረት፣ የንግድ ድርጅት፣ መኪና ወይንም ቤት እንዳይገዛ በጥብቅ እናሳስባለን። ይህን እያወቀ እነዚህን ወንጀለኞች የዘርፉት ሃብት በመግዛት የረዳ ወደፊት በህግ ይጠየቃል።

ኢትዮጲያ በነጻነቷ ለዘላለም ትኑር!

ነፃነት ለኢትዮጲያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.