ህወሓት ማመን ቀብሮ ነው – አምዶም ገብረስላሴ

it is so -satenaw

ህወሓት ለስልጣንዋ ዕድሜ መራዘም ስትል የማትሰራው ወንጀል፣ የማታጠፋው ሂወት፣ የማትሸጠው መሬት፣ የማትጠቀምበት ህዝብ ወዘተ የለታም።

ለህወሓት ከማንም በላይ ቅድምያ ሰጥታ የምትጠብቀው ስልጣን ብቻ ነው።

ህወሓት ብሄርዋ ስልጣን፣ ዜግነትዋ ስልጣን፣ ድንበርዋ ስልጣን፣ ሰብኣውነትዋ ስልጣን፣ ክብርዋ ስልጣን፣ ልማትዋ ስልጣን፣ ዕድገትዋ ስልጣን፣ ፍትህዋ ስልጣን ህዝቧ ስልጣን ነው።

የዚህ ማሳያ በድርቅ ግዜ የእርዳታ እህል መዝረፍና ሂወቱ እንዲያጣ ምክንያት እየሆነች ነው።

ዛሬ በሃገር ደረጃ 15 ሚልዮን ህዝብ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ተይዞ የመፅዋቾች እጅ ዘርግተዋል።

ድርቅ ለመቋቋምና የመስኖ ልማት ለማስፋፋት ተብሎ የመስኖና ውሃ ኢነርጂ ምኒስቴር በመላ ኣገሪቱ 105 ግድቦች ( 105 ለ 0 ማለት ነው) እንደሚገነቡ፣ ትግራይ ውስጥ ኣንዲት ግድብ እንደማትገደብና ከእቅዱ ውጭ እንደሆነች ገልፀውልናል።

ህወሓት ለትግራይ “ህዝብ ኣስርበህ ግዛ” የሚል ክፉ እቅድ ኣውጥታ እያሰቃየችው ነው።

ይኸው የዚህ ኣስርበህ ግዛ ፖሊሲዋ 1. 5 ሚልዮን የሴፍትኔት ፣ 1.2 ሚልዮን በድምሩ 2.7 ህዝብ የሚቀመስ ኣጥቶ እጆቹ ለምፅዋት እያቋመተ ነው ።

እናንተ ህወሓቶች ያልወደዳቹትና ያልረዳቹት ህዝብ ደግሞ በረሃብ እየሞተ ነው።

ከተመፅዋችነቱ ተላቆ እንዳሻቹት እንድትገዙትና በመሳርያነት እንድትጠቀሙበት ይሄው በመላ ኣገሪቱ ሊገነቡ የታሰቡትና ለመስኖ ልማት የሚውሉ ግድቦች ነፈጋቹት።

ህወሓት ህዝባችን ለስልጣንዋ መሳርያነት እንጂ የመልማት፣ ፍትህ የማግኘት፣ ዲሞክራሲያዊና ሰብኣዊ መብቱ የማክበር ፍላጎት የላትም።

ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ጀርባ ማለቀቅ የሁላችን ተጋሩና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜግች ግዴታና ሃላፊነት ነው።

ህወሓት ህዝባችን ከልማት እንዳገለለችው እኛም ከህዝባችን እናግልላት።

ጭቁን ህዝቦች በገዢዎች ሴራ እርስ በራሳችን መጠራጠርና መስጋት ኣቁመን ይሄ በ24 ዓመት ኣገዛዙ 15 ሚልዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በረሃብ፣ ሰለማዊ ተቃዋሚዎች በጥይት የሚቀላ፣ ለስልጣኑ ብቻ የሚጨነቅ መንግስት እንታገል።

 

ህወሓትን ማመን ቀብሮ ነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.