ዘራፊዎቹ የወያኔ ጄነራሎች ሴራ

የወያኔ ደንቆሮ ጀነራሎች የኢትዮጵያን ሠራዊት በሰላም አስከባሪነት ወደ ሶማሌ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳና ሌላም አፍሪካ አገር የሚሄዱት ወታደሮች ከ 1ሺ እስከ 1400 የአሜሪካ ዶላር በወር እንደሚከፈል እየታወቀ ከልዩ ጥቅማ ጥቅሞች በተጨማሪ እንደሚከፍል ነገር ግን የወያኔ ቱባ ጀነራሎች ለወታደሩ የሚከፍሉት እስከ 200 ዶላር እንደሆነና ከዚያ የተረፈው የወያኔ ጀነራሎች ኪስ እንደገባ ነው እናም ወንድሞቻችን እባካችሁ ከእንቅልፋችሁ ንቁ ሌላው ቀርቶ ለምሳሌ በሶማሌና በሌላም ቦታ ወታደሮቻችን ሲሰው አይተናል የተባበሩት መንግስታት ቢያንስ 100ሺ ዶላር የህይወት ካሳ እንደሚከፍል ነው ግን በዚህ የሰላም አስከባሪ የሞቱት ወገኖቻችን ይህ ካሳ ደርሶዋቸዋልን?

ሀቁን ከነርሱ ጋር አብሮ በአስተርጓሚነት ሄዶ የነበረው የአሁኑ እውቁ የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኰንን አብሮ መሄዱና ምን እንደተሰሩ ከእርሱ ሰኞ 24/08/2015 በተላለፈው ኢሳት ሬዲዮ ላይ ከ34ኛው ደቂቃ ጀምሮ በአንክሮ ተከታተሉት::

ይህን ጉድ በምንችለው መንገድ አገር ቤት ይህን ስርዓት በማገልገል ላይ ላሉ የሠራዊቱ አባላት ቤተሰቦቻችን የምናደርስበትን መንገድ ፈልጉ::

አያችሁ ወገኖች እኔ እድሜየ 57 ነው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ጊዜ 16 ዓመት ተማሪ ሆኘ ነው ለውጥ የመጣው ያደኩበት የወታደር አካባቢ ስለነበር ብዙ ጀነራሎችን አውቃለሁ እንኩዋን ቪላና ህንፃ ሊገነቡ የመንግስት ቤት ነበር የሚኖሩት፣ በደርግም ትምህርቴን ጨርሸ በቀድሞው ባህር ኃይል ሠራዊት ተቀጥሬ 10 ዓመት ከ10 ወር ከሀዲው ወያኔ በግፍ አገር እስከተቆጣጠረበት ድረስ አገልግያለሁ እናም እኔም የነበርኩበት ክፍልም ሆነ በምድር ጦርና አየር ኃይል የነበሩ ጀነራሎች እንዲህ የተጋነነ ቤት ያላቸው አላውቅም ዘመዴም ጀነራል ነበር እስራኤል፣ አሜሪካ ሄዶ የተማረ ነው ከእብሪተኛው የሲያድ ባሬ የሶማሌ ጦርነት ጀምሮ ለአገሩ ደሙን ያፈሰሰ፣ አጥንቱን የከሰከሰ የኢትዮጵያ የጀግና ኒሻን ተሸላሚ ነው ፖፕላሬ በሚባለው አካባቢ (ሽመልስ ሀብቴ ት/ቤት) አካባቢ በሚገኘው የመንግስት ትንሽ ቤት ውስጥ ነበር የሚኖረው::

እናም የአሁኖቹ ተደጋግሞ የተገለፀ ነው ከየት አምጥተው ነው ይኸ ሁሉ እናም ከላይ እንደተገለፀው በሰራዊቱ ህይወትና ደም ነግደው ነው፣ በህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ነው እነዚህ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ሰውንም የሚበሉ ጅቦች ናቸው ታዲያ ወገኔ የአገሬ ሰራዊት ሆይ ለማን ነው የምትሰቃየው? ለነርሱ ስልጣን ማራዘም አንተን ግደል እያሉ አባትህን፣ እናትህን፣ ወንድምህን፣ ልጅህን ሲያስገድሉህ ኖረዋል እናም አይበቃምን???

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.